Fana: At a Speed of Life!

በግዢ ዙሪያ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር የጋራ ምክክር መድረክ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እያካሄደ ነው። መንግስት በየዓመቱ ከሚመድበው ዓመታዊ በጀት 70 በመቶ የሚሆነው በግዢ የሚውል ሲሆን፥ በጀቱ ለታለመለት…

በአማራ ክልል ጉዳት የደረሰባቸው ኢንዱስትሪዎች በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ በቅንጅት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በግጭቱ ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸው አምራች ኢንዱስትሪዎች በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው ምክትል ሃላፊ ተፈሪ ታረቀኝ ለፋና…

የአፋር ክልል መስኅቦችን ለማስተዋወቅ ያለመ ጉብኝት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል የሚገኙ የመስኅብ ሥፍራዎችን ለማስተዋወቅ ያለመ የጉብኝት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው። መርሐ ግብሩ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል። የጉብኝት መዳረሻዎቹም፥ ኤርታሌ፣ ዳሎል፣ ዓሣአሌ የጨው ኃይቅ እና የጨው ንጣፍ…

በቡራዩ በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ ) ትናንት ምሽት 3:15 ላይ በሸገር ከተማ ቡራዩ በስፖንጅና በፕላስቲክ ውጤቶች ማምረቻ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ከባድ ጉዳት ደረሰ። በሦስት የእሳት አደጋ ሠራተኞች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱ ተመላክቷል። በንብረት ላይ የደረሰው የውድመት…

በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት በማምጣት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው ተማሪ ሚኪያስ አዳነ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተማሪ ሚኪያስ አዳነ በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈታና ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት በማምጣት ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል፡፡ የደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች ተማሪ ሚኪያስ አዳነ ስድስት መቶ ስልሳ…

ከ420 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የከረጢት ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ከ420 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በደብረ ማርቆስ ከተማ የተገነባውን የከረጢት ፋብሪካ መርቀው ሥራ አስጀመሩ። በምረቃ ስነ-ስርዓቱም የፌደራል፣የክልል፣የከተማ አስተዳደር የስራ ሃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች…

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ 160 ተጋላጭ ፍልሰተኞችን ወደ ሀገራቸው መለሰ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጅቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ቢሮ ጋር በመተባበር 160 ተጋላጭ ፍልሰተኞችን ወደ ሀገራቸው መልሷል፡፡ ፍልሰተኞቹ የጉዞ ሰነድ በማዘጋጀትና ግንዛቤ በማስጨበጥ ነው ፍልሰተኞችን ወደ…

ፍቅረኛውን ሳኒታይዘር በማርከፍከፍ በእሳት ተቃጥላ እንድትሞት አድርጓል የተባለው ተከሳሽ የሞት ፍርድ ተፈረደበት

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰብለ ንጉሴ የተባለች የፍቅር አጋሩን ሳኒታይዘር በማርከፍከፍ በእሳት ተቃጥላ እንድትሞት አድርጓል የተባለው ዳግማዊ አራጋው የሞት ፍርድ ተፈረደበት፡፡ በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮች…

36ኛው የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የአፍሪካ ሀገራት የነፃ ገበያ ትግበራ ማፋጠን ላይ ትኩረቱን ያደርጋል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የአፍሪካ ሀገራት የነፃ ገበያ ትግበራ ማፋጠን ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉባኤውን ለማካሄድ የተደረጉ ዝግጅቶችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።…

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ 745 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ለተሻለ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት እና በጎርፍ አደጋ ለተጎዱ የሚውል 745 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ። ባንኩ በዚህ ወቅት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች በኮቪድ-19፣ ከአየር ንብረት ጋር…