Fana: At a Speed of Life!

በሚቀጥሉት አስር ቀናት በሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ዝናቡ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየቀነሰ ይሄዳል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ከሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ እየተዳከሙ የሚሄዱበት ጊዜ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ዝናብ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየቀነሰ እንደሚሄድ የኢትዮጵያ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡…

በእስራኤል ጥገኝነት የሚጠይቁ ኤርትራውያን ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው በርካቶች መቁሰላቸው ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቴል አቪቭ የኤርትራ ኤምባሲ ያዘጋጀውን ዝግጅት በመቃወም የወጡ በመቶ የሚቆጠሩ ጥገኝነት ጠያቂ ኤርትራውያን ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው በርካቶች መቁሰላቸው ተነገረ። በግጭቱ የእስራኤል ፖሊስ መኮንኖችን ጨምሮ 140 ሰዎች መቁሰላቸውን…

ኢትዮጵያ የምታከናውነው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ለሌሎች የአፍሪካ አገራት ምሳሌ ይሆናል – አፍሪካ ኅብረት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የምታከናውነው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ለሌሎች የአፍሪካ አገራት ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የአፍሪካ ኅብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚና የዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር አምባሳደር ጆሴፋ ሳኮ ተናገሩ። ኮሚሽነር…

በመኸር ምርት ለአኩሪአተር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው – የግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015/16 የምርት ዘመን መንግስት ለአኩሪአተር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር)÷አኩሪአተር ለሀገር ውስጥ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ በተለይም ለዘይት…

ለክልሉ ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ቅድሚያ የሚሰጡ አመራሮችን ወደ ፊት ለማምጣት በትኩረት እንሰራለን -የአማራ ክልል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ ለሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ቅድሚያ የሚሰጡ አመራሮችን በየደረጃው ወደ ፊት ለማምጣት በትኩረት እንሰራለን ሲል የአማራ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። የክልሉ መንግስት የጸጥታ ተቋማትን ለማጠናከር የሰላምና ጸጥታ፣ ፖሊስ…

ሜዲካል ጎዝ እና የወረቀት ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሜዲካል ጎዝ እና የወረቀት ምርቶችን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እየተሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የኢንድስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በአዳማ ከተማ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝተዋል፡፡…

በሶስትዮሽ ድርድሩ የኢትዮጵያን የመልማት መብት የማይገድብ ስምምነት ላይ እንዲደረስ በጥንቃቄ እየተሰራ ነው- ስለሺ በቀለ(ዶ/ር ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር የኢትዮጵያን የመልማት መብት የማይገድብ ስምምነት ላይ እንዲደረስ በጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን መሪና በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ።…

በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፉ የአትሌቲክስ ቡድን አባላት የማበረታቻ ሽልማት እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፉ የአትሌቲክስ ቡድን አባላት የማበረታቻ ሽልማት እየሰጠ ነው። በመርሐ ግብሩ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳን ጨምሮ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ…

አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ከተለያዩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይቱ ላይ÷ በክልሉና በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ፣ የፖለቲካ እና የጸጥታ ጉዳዮችና ቀጣይ እቅዶች እንዲሁም…

ኮያንግፖኦክ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ አበባ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል ለመስጠት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮያንግፖኦክ ዩኒቨርሲቲ የተሻለ ውጤት ለሚያስመዘግቡ ለአዲስ አበባ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል ለመስጠት ተስማማ። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በደቡብ ኮሪያ ቹንቾን ከተማ ከሚገኘው ታዋቂው ኮያንግፖኦክ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ኪም…