Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለዊሊያም ሩቶ በዓለ ሲመት ናይሮቢ ገቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲሱ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በዓለ ሲመት ለመታደም ኬንያ፣ ናይሮቢ ገቡ። ዊሊያም ሩቶ በቅርቡ በሀገሪቱ በተካሄደ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የኬንያ አምስተኛ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸው ይታወቃል።…

መዲናዋን ሰላማዊ የማድረግ የጋራ እንቅስቃሴያችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ጥሪዬን አቀርባለሁ-ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተማችንንና የዙርያዋን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ሰላማዊ እና የተረጋጋ የማድረግ የጋራ እንቅስቃሴ ስራችንን አጠናክረን እንቀጥል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ። ከንቲባዋ ይህን በማድረግ የጠላትን ከንቱ ምኞት ማክሸፋችንን ልንቀጥል ይግባል…

ዊሊያም ሩቶ የኬንያ ፕሬዚዳንት በመሆን ቃለ-መሓላ ፈጸሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዊሊያም ሩቶ 5ኛው የኬንያ ፕሬዚዳንት በመሆን ቃለ-መሓላ ፈፀሙ። በበዓለ ሲመቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት መሪዎችና ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ሩቶ ባለፈው ወር በተካሄደው ምርጫ ከ50 በመቶ…

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ለአዲስ አመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መኸመት የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ሊቀመንበሩ በመልዕክታቸው፥ "አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የሰላም፣…

የድሬዳዋ አስተዳደር በአፋር ለሚገኙ መከላከያ ሰራዊት የቁም እንስሳቶችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር በአፋር ግንባር ጭፍራ ለሚገኙ መከላከያ ሰራዊት ለበዓል የቁም እንስሳቶችን ድጋፍ አደረገ ፡፡ የድሬዳዋ ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት ተጠሪና የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፅ/ቤት ሀላፊ ኢብራሂም…

ከንቲባ አዳነች በተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በመገኘት በዓሉን በጋራ አሳለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ በቂርቆስ ክ/ከተማ አዲስ በተገነባው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማእከል በዓሉን በጋራ አሳልፈዋል፡፡ ከንቲባዋ ከቢኬጂ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን ነው በዓሉን ከምገባ ማዕከሉ ተጠቃሚዎች…

በ2015 በጀት ዓመት ከቡና ምርት 2 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት ታቅዷል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት ከቡና የውጪ ንግድ 2 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት መታቀዱ ተገለፀ፡፡ ባለፈው በጀት ዓመት 4 ነጥብ 12 ቢሊየን ዶላር ከውጪ ንግድ የተገኘ ሲሆን÷ ከዚህ ውስጥ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላሩ ከቡና የወጪ ንግድ የተገኘ መሆኑ…

የመንግስት የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶችን በቴሌ ብር መክፈል የሚያስችል ስርዓት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ክፍያ የሚያስፈልጋቸውን የመንግስት የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶች በቴሌ ብር መክፈል የሚያስችል ስርዓት ተጀምሯል፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የሂሳብ አያያዝ ኦዲት ቦርድ በኦንላይን የሚሰጡ የመንግስት…

ፋሲል ከነማ ቡማሙሩን 3 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪከ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ቅድመ ማጣሪያ ከቡሩንዲው ክለብ ቡማሙሩ ጋር የተጫወተው ፋሲል ከነማ 3 ለ ዐ አሸንፏል። በባህርዳር ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አለም ብርሃን ይግዛው፣ፈቃዱ አለሙ እና ታፈሰ ሰለሞን የማሸነፊያ ጎሎችን አስቆጥረዋል።…

የሐረሪ ክልል ለ59 ለሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ59 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል፡፡ የክልሉ መንግስት ይቅርታ ያደረገው የይቅርታ መስፈርቱን አሟልተው ለተገኙ 59 ታራሚዎች መሆኑን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡…