Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የእውቅና እና ምስጋና መርሐ ግብር ተካሔደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ በ2015 ዓ.ም በተመዘገቡ ስኬቶችና የለውጥ ክንውኖች ዙሪያ የእውቅና እና የምስጋና መርሐ ግብር ተካሔደ ፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ፣…

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለሚያደርገው ተቋማዊ ሪፎርምና ሕግ ማውጣት ስራ በጥናትና ምርምር የተደገፈ ስራ እየተሰራ ነው- አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሚያደርገው ተቋማዊ ሪፎርምና ህግ ማውጣት ስራ በጥናትና ምርምር የተደገፈ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛው የፓርላማ ጥናትና ምርምር…

በኢንዱስትሪ ፓርኮች በተፈጠረ የገበያ ትስስር ከ300 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላው ኢትዮጵያ በተገነቡ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተፈጠረ የገበያ ትስስር ከ300 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ፡ የኮርፖሬሽኑ የማርኬቲንግና ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘመን ጁነዲን…

በጸጥታ አካላት ላይ ተኩስ ከፍተው ነበር የተባሉ 20 ተጠርጣሪዎች ላይ ለምርመራ ማጣሪያ የ14 ቀን ጊዜ ተፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍርድ ቤቱ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን በመያዝ በፀጥታ አካላት ላይ ተኩስ ከፍተው ነበር የተባሉ 20 ተጠርጣሪዎች ላይ የምርመራ ማጣሪያ እንዲደረግ የ14 ቀን ጊዜ ፈቅዷል፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በመርማሪ…

የወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቅናቄ ነገ በአሶሳ ከተማ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቅናቄ ነገ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ እንደሚጀመር የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አስታወቀ፡፡ የሊጉ ምክትል ፕሬዚዳንትና የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አባንግ ኩመዳን በሰጡት መግለጫ…

ኢትዮጵያ በ3ኛው የቻይና-አፍሪካ የንግድ እና ኢኮኖሚ ኤክስፖ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በ3ኛው ቻይና-አፍሪካ የንግድ እና ኢኮኖሚ ኤክስፖ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡ በቻይና ሁናን እየተካሄደ በሚገኘው ኤክስፖ ላይ የ53 አፍሪካ ሀገራት ተወካዮች እና የበርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች አመራሮች…

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን የሰብዓዊ መብት ጥስት ክስ በማንሳት ምንም የፋይናንስ ድጋፍ ክልከላ እንደማይደረግባት አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን የሰብዓዊ መብት ጥስት ክስ በማንሳት ሀገሪቱ ከዚህ በኋላ ምንም አይነት የፋይናንስ ድጋፍና አቅርቦት ክልከላ እንደማይደረግባት አስታወቀች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰነድን ዋቢ አድርጎ ፎሬይን ፖሊሲ…

ሩሲያ ከምዕራባውን ጋር ለመፎካከር ዝግጁ ናት አሉ ፕሬዚዳንት ፑቲን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በየትኛውም ዘርፍ ከምዕራባውን ጋር ለመፎካከር ዝግጁ ናት ሲሉ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናገሩ፡፡ ፕሬዚዳንት ፑቲን“ለመጪው ጊዜ አዲስ ሃሳብ” በተሰኘ ፎረም ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር÷የምዕራውያን ሀገራት በሩሲያ ላይ የጣሉት…

በፕሪሚየር ሊጉ ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገዋል፡፡ ድሬዳዋ ከተማ እና አርባ ምንጭ ከተማ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የድሬዳዋ…

የሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከሰኔ 23 ቀን 2015 እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡ በዚሁ መሠረት፦ 1. ቤንዚን ……………………………………… ብር 69.52 በሊትር…