Fana: At a Speed of Life!

ቋሚ ኮሚቴው የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አገልግሎት አሰጣጡን እንዲያሻሽል አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አገልግሎት አሰጣጡን እንዲያሻሽል አሳሰበ፡፡   የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር ዶክተር መኩሪያ ኃይሌ…

በመዲናዋ በ2015 በጀት ዓመት ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በ2015 በጀት ዓመት ነባር ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል በልዩ ትኩረት የሚሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ገለጸ። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት በጀት አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ…

አቶ ደመቀ መኮንን ከቡርኪናፋሶ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከቡርኪናፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦሊቪያ ሩምባ ጋር ተወያይተዋል፡፡ አቶ ደመቀ ፥ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የረጅም ጊዜ ግንኙነት ከቅኝ ግዛት ዘመን ጀምሮ የተጀመረ መሆኑን…

በአረንጓዴ አሻራ እየተመዘገበ ያለውን ስኬት በገቢ አሰባሰቡ በመድገም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በትጋት እንሰራለን- ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን እና የገቢዎች ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች በሰበታ አዋስ ደበል ተራራ ለአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ችግኝ ተክለዋል፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ÷የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ የኮሚሽኑ…

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ1ቢሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ1ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡ ጽሕፈት ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው…

አየርላንድ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል አንድ ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አየርላንድ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል ተጨማሪ አንድ ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች፡፡ አየርላንድ ያደረገችው ድጋፍ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ እና አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚውል መሆኑ…

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ15 ዓመት የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ አዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለዜጎች የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ያሻሽላል ያለውን የ15 ዓመት የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀቱን የክልሉ የጤና ቢሮ አስታወቀ። ፍኖተ ካርታውን የሚያስተዋውቅ የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት…

በሁመራ ከተማ በጦርነት ለተጎዱ ነዋሪዎች ከ12 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ማኅበራዊና ልማት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከካሪታስ ስዊዘርላንድ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር በሁመራ ከተማ በጦርነት ለተጎዱ ነዋሪዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡ በካሪታስ ስዊዘርላንድ…

በሲዳማ ክልል የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአለታ ጩኮ ወረዳ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልላዊ መንግስት የእርሻ እና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አስተባባሪነት የዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ማስጀመሪያ በአለታ ጩኮ ወረዳ ቴሶ ቀበሌ እየተካሄደ ነው።   በሲዳማ ክልል አለታ ጩኮ ወረዳ ቴሶ ቀበሌ ቦሪቴ…

ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ እና የክልሉ ካቢኔ አባላት በሰሜን ሸዋ ዞን የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ እና የክልሉ ካቢኔ አባላት በሰሜን ሸዋ ዞን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂደዋል፡፡ በመርሐ ግብሩ በሰሜን ሸዋ ዞን ደረጃ ከ270 ሚሊየን በላይ ችግኝን ለመትከል እንደታቀደና…