Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በኢትዮጵያ ከቱርክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በኢትዮጵያ ከቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ ጋር በሰመራ ተወያይተዋል፡፡   በውይይታቸውም በአፋር ክልል ወቅታዊ ሁኔታ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ነው የተገለጸው፡፡…

ቱርክ የስዊዲንና ፊንላንድ ኔቶን የመቀላቀል ፍላጎት በአዎንታ እንደማትመለከት ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ስዊዲንና ፊንላንድ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ሀገር ለመሆን ላሳዩት ፍላጎት አዎንታዊ አስተያየት እንደሌላቸው አስታወቁ። ለዓመታት ከብዙ መሰል ህብረቶች ገለልተኛ…

ጠ/ ሚ ዐቢይ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ የሃላፊነት ጊዜያቸው ስኬታማ እንዲሆን ተመኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሆነው በመሾማቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፥ ሼክ…

አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በጦርነቱ ተሳትፎ ያልነበረቸው 7 ሺህ የሚጠጉ ንፁሃንን መግደሉን ጥናት አመለከተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራ ክልል በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በጦርነቱ ምንም አይነት ተሳትፎ ያልነበረቸው 6 ሺህ 985 ንፁሃን ዜጎችን መግደሉን ጥናት አመለከተ፡፡ አሸባሪ ቡድኑ በአማራ ክልል በወረራ በቆየባቸው አካባቢዎች ያደረሰው…

አቶ ሙስጠፌ የኮንትሮባንድ ንግድን መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከጸጥታ አካላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከፌደራልና ከክልል ፀጥታ ሃይሎች አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በሶማሌ ክልል የሚስተዋለውን የኮንትሮባንድ ንግድ መከላከል በሚቻልበት ጉዳይ ላይ መክረዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም…

የመዲናዋን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ ኅብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ መቀጠል አለበት-ፖሊስ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ሠላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ ኅብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ።   የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ…

የአጋሮ ከተማ ነዋሪዎች ሃይማኖትን ከለላ በማድረግ ሊፈጸም የነበረን ጥፋት አከሸፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአጋሮ ከተማ ነዋሪዎች ሃይማኖትን ከለላ በማድረግ ሊፈፀም የነበረን ጥፋት ከከተማው የጸጥታና አስተዳደር አካላት ጋር በመቀናጀት ማክሸፋቸው ተገልጿል፡፡   የአጋሮ ከተማ ከንቲባ አቶ ነዚፍ መሐመድ አሚን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት…

ጠ/ሚ ዐቢይ በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ለተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች አልጋ ወራሽ…

የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ73 ዓመታቸው ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፡፡…

አሰልጣኝ ፍሬው ሃይለገብርኤል የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ፍሬው ሃይለገብርኤል የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾመዋል፡፡ በዚህ መሰረትም ከቀናት በኋላ በዩጋንዳ አስተናጋጅንት ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የሴካፋ ሴቶች እግርኳስ ውድድር ላይ ሉሲዎቹ በአሰልጣኝ ፍሬው…