Fana: At a Speed of Life!

ከ12 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2014/15 የሰብል ዘመን የሚውል ከ12 ሚሊየን ኩንታል በላይ ከውጭ ሀገር የተገዛ የአፈር ማዳበሪያ ከጥር 2014 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ መሆኑን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ገለጸ። ለዘንድሮው የምርት ዘመን የሚውል…

የራያ የወሰንና የማንነት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሠረት እንደሚመለስ የፌዴሬሽን ም/ቤት ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የራያ የወሰንና የማንነት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሠረት እንደሚመለስ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለጸ፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ለራያ ሕዝብ ተወካዮች ላቀረቡት ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ፥ የራያ ሕዝብ ጥያቄ በሕገ…

ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ለሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ ማረፊያ ቦታ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ለሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የማረፊያ ቦታ መዘጋጀቱን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን በጊዜያዊነት የሚያርፉበት ቦታ በተለምዶ ወሰን ሁለት ተብሎ…

የቤንዚን አቅርቦት ችግርን በጥቂት ቀናት ውስጥ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የተፈጠረውን የቤንዚን አቅርቦት ችግር በጥቂት ቀናት ውስጥ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ ፋና ብሮካስቲንግ ኮርፖሬት በአዲስ አበባ ከተማ ባደረገው ቅኝት ረጃጅም የተሽከርካሪ…

የጂቡቲው ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ የነበራቸውን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ አገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ በኢትዮጵያ የያደረጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ አገራቸው ተመለሱ። የጅቡቲው ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ የገቡት…

ሚኒስቴሩ በሻማ፣ ዘይት ፣ ሳሙና እና ካልሲ ማምረት ሥራ ያሰለጠናቸውን 110 ወጣቶች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የጀርመን ትብብር ልማት (ጂ.አይ. ዜድ) ከተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በሻማ ፣ ዘይት ፣ ሳሙና እና ካልሲ ማምረት ሥራ ያሰለጠናቸውን 110 ወጣቶች አስመረቀ፡፡ በምረቃ ሥነስርዓቱ ላይ የተገኙት የሥራ…

መንግሥት ቀዳሚ ትኩረት በሰጠባቸው የግብርና ልማት ዘርፎች ላይ የልማት አጋሮች ትብብር አስፈላጊ መሆኑን ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት ቀዳሚ ትኩረት በሰጠባቸው የግብርና ልማት ዘርፎች ላይ የልማት አጋሮች ትብብር አስፈላጊ መሆኑን የኢፌዴሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለፁ። ሚኒስትሯ ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ማዊራ…

ድርጅቱ በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በባህር ትራንስፖርትና የገቢ እቃዎች ላይ ለተፈጠረው ጫና አማራጮች እየተፈለጉ ነው አለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና የገቢ እቃዎች ማጓጓዝ ላይ ለፈጠረው ጫና አማራጮች እየተፈለጉ መሆኑን የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ገለጸ። ጦርነቱ ከተጀመረ አንድ ወር ባለፈው የሩሲያና…

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የብሔረሰብ ስያሜው “ቤኒሻንጉል” እንዲሆን ወሰነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ከዚህ ቀደም በርታ ተብሎ ሲጠራ የነበረውን የብሔረሰብ መጠሪያ "ቤኒሻንጉል" ተብሎ እንዲሰየም የቀረበለትን የብሔረሰብ መጠሪያ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ፡፡ የብሔረሰቡን ስያሜ በተመለከተ የብሔረሰብ…

ቦርዱ ፓርቲዎች ላቀረቧቸው አቤቱታዎች ምላሽ ለመስጠት አጣሪ ቡድን አዋቅሮ ምርመራ ማከናወኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ፓርቲዎች ላቀረቧቸው አቤቱታዎች ምላሽ ለመስጠት አጣሪ ቡድን አዋቅሮ ሰፊ የምርመራ ሥራ ማከናወኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። ቦርዱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተለያዩ…