Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዓለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነብርሀን ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነብርሀን ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የዓለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነብርሀንን ከ45 ዓመት በፊት በአውሮፓ የኢትዮጵያ ተማሪዎች…

የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ መስተዳድር የስራ ኃላፊዎች ሀዋሳ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ መስተዳድር የስራ ኃላፊዎች ለሰዳማ ክልል የምስረታ ስነስርዓት ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል። የሲዳማ ክልል የምሥረታ ሥነ- ሥርዓት በነገው እለት የሚካሄድ ሲሆን የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ መስተዳድር የስራ ኃላፊዎች…

ጅማ አባ ጅፋር ሲዳማ ቡናን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጅማ አባ ጅፋር ሲዳማ ቡናን 1ለ 0 አሸነፈ፡፡ ሱራፌል አወል ለጅማ አባ ጅፋር ብቻኛዋን ጎል አስቆጥሯል፡፡ ዛሬ 9 ሰዓት ሃዋሳ ከተማ እና ፋሲል ከተማ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ…

በሲዳማ ክልል 125ኛው የአድዋ ድል በአል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ደረጃ 125ኛው የአድዋ ድል በአል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው። በዓሉ ከሲዳማ ባህል ፌስቲቫል ጋር በጥምረት እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን፤ በዓሉን አስመልክቶ የሲዳማን ባህል የሚያንፀባርቁ የተለያዩ ቁሳቁሶችና አልባሳት እንዲሁም…

የባቡር ሀዲድ ሲዘርፉ የነበሩ ዘጠኝ ግለሰቦች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳው ከአዲስ አበባ ጂቡቲ የሚያገናኘውን ነባሩን የባቡር ሀዲድ መስመር ብረት ሲዘርፉ የነበሩ ዘጠኝ ግለሰቦችን እጅ ከፍጅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ። የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር…

የድሬደዋ ብልፅግና ፓርቲ የፓርቲውን የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት እና ማኒፌስቶ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የድሬደዋ ብልፅግና ፓርቲ የፓርቲውን የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት እና ማኒፌስቶ ይፋ አደረገ። "ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለጋራ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል በመጪው ሀገራዊ ምርጫ ላይ የሚሳተፈው ፓርቲው ለአባላቱ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቱን እና…

ሃላላ ኬላ ተነግሮ የማይጠገብ ታሪክ ያለው ስፍራ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሃላላ ኬላ ተነግሮ የማይጠገብ ታሪክ ያለው ስፍራ mሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በገበታ ለሃገር መረሃ-ግብር የኮይሻ ፕሮጀክትን የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታን ለማስጀመር በዳውሮ ዞን በመገኘት ንግግር አድርገዋል፡፡…

የሀረር ሰዎች ለሰዎች የአግሮ ቴክኒክና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ 183 ሰልጣኞችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሀረር ሰዎች ለሰዎች የአግሮ ቴክኒክና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን 183 ሰልጣኞችን በዲግሪ አስመረቀ። በዶ/ር ካርል ሄንዝ በም የተመሰረተውና በተለያዩ የአግሮ ቴክኒክና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ተማሪዎችን ተቀብሎ ከ1984 ዓ.ም…

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የ2013 የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈፃፀም እየተገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል እና የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ…

የሲዳማ ክልል የምስረታ በዓልን አስመልክቶ ልዩ የስፖርት እንቅስቃሴና ውድድር በሐዋሳ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልል የምስረታ በዓልን አስመልክቶ ልዩ የስፖርት እንቅስቃሴና ውድድር በሐዋሳ ከተማ ተካሄደ። በነገው ዕለት የካቲት 15/2013 ዓም የሚከበረውን የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ይፋዊ የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በሲዳማ ብሔራዊ…