የሀገር ውስጥ ዜና የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ሴክሬታሪያት ዋና ጸሐፊ አዲስ አበባ ገቡ Meseret Awoke Aug 29, 2024 0 አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ሴክሬታሪያት ዋና ጸሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ለዋና ጸሃፊው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴዔታ ያስሚን ወሐብረቢ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል…
የሀገር ውስጥ ዜና በስልጤ ዞን ለጎርፍ አደጋ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ Meseret Awoke Aug 29, 2024 0 አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስልጤ ዞን በተደጋጋሚ ለሚከሰተው የጎርፍ አደጋ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። የክልሉ አደጋ ስጋት ኮሚሽነር ማዕረጉ ማቴዎስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት…
የሀገር ውስጥ ዜና በዘንድሮው የመኸር ወቅት 10 ሚሊየን ሄክታር መሬት በክላስተር ለምቷል – የግብርና ሚኒስቴር Meseret Awoke Aug 28, 2024 0 አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው የመኸር ወቅት 10 ሚሊየን ሄክታር መሬት በክላስተር መልማቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት በግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ኢሳያስ ለማ፥ በ2016/17 የመኸር…
ዓለምአቀፋዊ ዜና ኢራን ከአሜሪካ ጋር በኒውክሌር ዙሪያ ለመደራደር በሯን ከፈተች Meseret Awoke Aug 28, 2024 0 አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን ከአሜሪካ ጋር በኒውክሌር ዙሪያ ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች፡፡ የኢራን ከፍተኛ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ በቴህራን የኒውክሌር ፕሮግራም ላይ ከአሜሪካ ጋር እንደገና ለመደራደር ለሀገሪቱ መንግስት "ምንም እንቅፋት የለም" ብለዋል።…
ጤና 10 ሺህ የዝንጀሮ ፈንጣጣ መከላከያ ክትባት ናይጄሪያ ደረሰ Meseret Awoke Aug 28, 2024 0 አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 10 ሺህ የዝንጀሮ ፈንጣጣ መከላከያ ክትባት ናይጄሪያ ደረሰ። የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የዓለም የጤና ስጋት መሆኑ ከተገለጸ ወዲህ ክትባቱን በመረከብ ናይጄሪያ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር መሆኗ ተገልጿል። በዓለም የጤና ድርጅት የዓለም የጤና…
የሀገር ውስጥ ዜና ገቢሳ ኤጀታ (ፕ/ር) የዓመቱ የሰብል ልማት ተመራማሪ ተብለው ተመረጡ Meseret Awoke Aug 28, 2024 0 አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ስመጥር ፑርዱ ዩኒቨርሲቲ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ገቢሳ ኤጀታን (ፕ/ር) በአከናወኑት የግብርና ምርምር ሥራ የዓመቱ የሰብል ልማት ተመራማሪ አድርጎ መርጧል፡፡ ገቢሳ ኤጀታ (ፕ/ር) በተለያየ ጊዜ በአካሄዱት ምርምር “ሃይብሪድ” የሆኑ የማሽላ…
የሀገር ውስጥ ዜና ክልሉ የበቆሎ ምርጥ ዘር ፍላጎቱን በራሱ አቅም ለመሸፈን እየሠራ መሆኑን አስታወቀ Meseret Awoke Aug 28, 2024 0 አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዚህ ዓመት የበቆሎ ምርጥ ዘር ፍላጎቱን ከ50 በመቶ በላይ በራሱ አቅም ለመሸፈን እየሠራ መሆኑን የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ ላለፉት ዓመታት የሚያስፈልገው ምርጥ ዘር ከ70 በመቶ በላይ የሚሸፈነው በሌሎች ክልሎች…
ዓለምአቀፋዊ ዜና አሜሪካ ከፌስቡክ ላይ የኮቪድ-19 የተወሰኑ ይዘቶች እንዲነሱ ግፊት አድርጋ ነበር ተባለ Meseret Awoke Aug 27, 2024 0 አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አሥተዳደር በ2021 የኮቪድ-19 የተወሰኑ ይዘቶች ከፌስቡክ እንዲወገዱ ለወራት በተደጋጋሚ ግፊት ማድረጉን የሜታ ኩባንያ መስራች ማርክ ዙከር በርግ አመላከቱ፡፡ ዙከር በርግ ለሀገሪቱ ምክር ቤት የፍትሕ ኮሚቴ በጻፉት ደብዳቤ÷…
የሀገር ውስጥ ዜና የግድቡ ተጨማሪ ተርባይኖች ወደ ሥራ መግባት ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኤሌክትሪክ ኃይል ለማስተሳሰር የምታደርገው ጥረት አመላካች ነው ተባለ Meseret Awoke Aug 27, 2024 0 አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016(ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጨማሪ ሁለት ተርባይኖች ወደ ሥራ መግባት ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኤሌክትሪክ ኃይል ለማስተሳሰር የምታደርገው ጥረት አመላካች ነው ሲሉ የቀድሞ የግድቡ ተደራዳሪና የውኃ ኃብት ተመራማሪው ፈቅ አሕመድ ነጋሽ ገለጹ።…
የሀገር ውስጥ ዜና 50 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት ወደሀገር ውስጥ እየተጓጓዘ ነው Meseret Awoke Aug 26, 2024 0 አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 50 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እየተጓጓዘ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ከጅቡቲ ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተጓጓዘ ያለው የምግብ ዘይት የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል እና ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ታስቦ…