Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል አደጋን ቀድሞ መከላከል የሚያስችል ከ220 ሚሊየን ብር በላይ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ከመድረሳቸው በፊት ቀድሞ መከላከል የሚያስችል ከ220 ሚሊየን ብር በላይ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ። ከነገ ጀምሮ ወደ ሥራ የሚገባው ይህ ፕሮጀክት በክልሉ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የማይበገር…

የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በሶስት ዓመት ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በሶስት ዓመት ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገለፁ። 2 ሺህ 160 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ግድብ…

የትምህርት ቤት አመራሮችን አቅም ለማሳደግ የስልጠና ማንዋል ተዘጋጅቷል -ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች የስልጠና ሂደት ለማሻሻል የሚያስችሉ የማሰልጠኛ ማንዋሎች መዘጋጀታቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። የማሰልጠኛ ማንዋሉ ትምህርት ሚኒስቴር ከኤጁኬሽን ደቨሎፕመንት ትረስት ከተሰኘ…

በአዲስ አበባ በግለሰብ ቤት የተከማቸ ከ2 ሚሊየን በላይ አዲሱ የብር ኖት ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በግለሰብ ቤት ውስጥ የተከማቸ ከ2 ሚሊየን በላይ አዲሱ የብር ኖት መያዙን ፖሊስ አስታወቀ። ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ዶምቦስኮ ትምህርት ቤት…

የታላቁ ህዳሴ ግድብ አጭር የፅሁፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ 3ኛ ዙር ሁለተኛ ተሸላሚ መኪናቸውን ተረከቡ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የታላቁ ህዳሴ ግድብ አጭር የፅሁፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ የ3ኛ ዙር ሁለተኛ ተሸላሚ መኪናቸውን ተረከቡ፡፡ አሸናፊዋ ወይዘሮ አሰፋሽ አፈወርቅ ከኢሉባቡር በቾ ወረዳ ሲሆኑ ዘመናዊ ቢዋይ ዲ መኪና ተረክበዋል። የስልክ መልዕክት የገቢ…

በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት የተካሄዱ ለውጦችን የዳሰሰ መፅሐፍ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በኢትዮጵያ የተከናወነውን የፖለቲካ ለውጥ ሂደትና ቀጣይ አቅጣጫዎች የሚያመላክት መጽሐፍ ተመርቋል።   በእንግሊዝኛ ቋንቋ "Ethiopia in the wake of political…

በአዲስ አበባ በስፖንጅ ፋብሪካ ውስጥ የተነሳ እሣት ንብረት አወደመ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ በስፖንጅ ፋብሪካ ውስጥ የተነሳ እሣት ከ500 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ማውደሙን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለፀ። በክፍለ ከተማው ወረዳ 3 ራስ ደስታ አካባቢ በአንድ ሺህ ካሬ ሜትር…

በብሔር አስተዳደር፣ በብዝኅነት አያያዝ እና በሃይማኖቶች የጋራ እሴት ላይ ያተኮረ ኮንፈረንስ በጅማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በብሔር አስተዳደር፣ በብዝኅነት አያያዝ እና በሃይማኖቶች የጋራ እሴት ላይ ያተኮረ ኮንፈረንስ በጅማ እየተካሄደ ነው። ኮንፈረንሱ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑ…

የኢትዮጵያና የቻይና ግንኙነት ጥሩ የትብብር ማሳያ ነው – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የኢትዮጵያና የቻይና ግንኙነት ለአፍሪካ ቻይና ትብብር ጥሩ ማሳያ መሆኑን ተናገሩ። አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከሺንዋ ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ ኢትዮጵያ እና ቻይና ላለፉት 50 ዓመታት…

የተመራቂ ተማሪዎች የቅበላ መርሃ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2013 የትምህርት ዘመን እንዲቀጥል በተወሰነው መሠረት የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በመጀመሪያው ዙር የተመራቂ ተማሪዎች የቅበላ መርሃ ግብር ይፋ ተደረገ። በዚሁ መሰረት፡- 1. ጥቅምት 23 እና 24 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ…