Fana: At a Speed of Life!

የህዝቦችን ግንኙነት ለማጠናከር የባህልና ስፖርት ዘርፍ አቅምን መጠቀም ይገባል-ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝቦችን የእርስ በእርስ ግንኙነት ለማጠናከር የባህልና ስፖርት ዘርፍ አቅምን መጠቀም ይገባል ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ተናገሩ፡፡ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ጋር በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ…

ኢትዮጵያና ቼክ ሪፐብሊክ በከባድ ኢንዱስትሪ ማምረቻዎችና በግብርና  በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ቼክ ሪፐብሊክ በከባድ ኢንዱስትሪ ማምረቻዎች፣ በግብርና ፣በመከላከያ እና በሙዚየም ጉዳዮች በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኢትዮጵያ የቼክ ሪፐብሊክ…

የዓድዋ ድል መታሰቢያ አዲስ አበባን የኮንፈረንስና የስበት ማዕከል እያደረጋት ይገኛል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን በማስተናገድ አዲስ አበባን የኮንፈረንስና የስበት ማዕከል እያደረገ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡ ከንቲባዋ ባስተላለፉት መልዕከት÷ በኢትዮጵያ፣ አፍሪካ ህብረትና…

ዶናልድ ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው ምን ይተገብራሉ?

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በአብላጫ ድምፅ በማሸነፍ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው ሰባት ዋና ዋና ፖሊሲዎችን ለማስፈፀም ቃል ገብተዋል፡፡ ትራምፕ ወደ ኋይት ሀውስ ሲመለሱ በኢሚግሬሽን፣ በኢኮኖሚ፣…

በኢንዱስትሪ ፓርኮች የቻይና ባለሀብቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንዱስትሪ ፓርኮች የቻይና ባለሀብቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከቻይና-አፍሪካ ንግድ ምክር ቤት የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ተወያይቷል። በውይይቱ…

ዶናልድ ትራምፕ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አነጋጋሪውና አወዛጋቢው ሲሉ ብዙዎች የሚጠሯቸው የ78 ዓመቱ ዶናልድ ጆን ትራምፕ በፈረንጆቹ 1946 ነበር ምድርን የተቀላቀሉት፡፡ አሜሪካዊው ፖለቲከኛ የሚዲያ ሰውና ነጋዴም ናቸው፡፡ በኢኮኖሚክስ ዲግሪያቸውን ከፔንሲልቫኒያ ዩኒቨርሲቲ በ1968…

የሀገራት መሪዎች ለፕሬዚዳንት ትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት እያስተላለፉ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ሀገራት መሪዎች የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን ላሸነፉት ዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክታቸውን እያስተላለፉ ይገኛሉ። ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ለመሆን የሚያስችላቸውን ድምጽ ማግኘታቸውን ተከትሎ የእስራኤል ጠቅላይ…

የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ቀጥለው ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ አራተኛ ዙር ሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይካሄዳሉ። ምሽት 2 ሠዓት ከ45 ላይ የቤልጂየሙ ክለብ ብሩጅ ከእንግሊዙ አስቶንቪላ፤ እንዲሁም የዩክሬኑ ሻካታር ዶኔስክ ከስዊዘርላንዱ ያንግ ቦይስ ጋር ይጫወታሉ፡፡…

በአማራ ክልል አነስተኛ ገቢ ላላቸውን ወገኖች ቤት ለመገንባት የተያዘው እቅድ ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ባለፉት አምስት ዓመታት አነስተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች የመኖሪያ ቤት ለመገንባት የተያዘው እቅድ ውጤታማ እየሆነ እንደሚገኝ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ተናገሩ። ርዕሰ መስተዳደሩ በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ያለውን…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤ350-1000 አውሮፕላን ከኤር ባስ ተረከበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤ350-1000 "Ethiopia land of origins" የሚል ስያሜ የተሰጠውን የመንገደኞች አውሮፕላን ዛሬ ከኤር ባስ የአውሮፕላን ኩባንያ ተረክቧል ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ…