Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ሁኔታን አስመልክቶ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ የተመራ የፌዴራል መንግስት ልዑክ በአማራ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ ከክልሉ መንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይቷል፡፡ በውይይት መድረኩ  የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ…

ኢትዮጵያ በሩሲያው ዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ንግድ ትርኢት ላይ ተሳተፈች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በ2023 የሩሲያው ዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ንግድ ትርኢት ላይ መሳተፏን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የንግድ ትርዒቱ ዘላቂ ምርትና ምርታማነትን እንዲሁም የማሻሻያ ስትራቴጂዎች ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡ በተለይም ለከተሞች እና…

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በጅማ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ሒደትን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመራቂ ተማሪዎችን የመውጫ ፈተና አሰጣጥ ሒደት ተመልክተዋል፡፡ ሚኒስትሩ በፈተና ክፍሎች ተዘዋውረው ሒደቱን በመመልከት ተፈታኞቹን፣ ተቆጣጣሪዎችን እና አስተባባሪዎችን  አበረታተዋል፡፡…

ማኅበሩ ለሱዳን ስደተኞች ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ለሱዳን ስደተኞች እስከአሁን 10 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ፡፡ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀልና የቀይ ጨረቃ ፌደሬሽን አስተዳደር ሰሞኑን በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ያደረጉትን ጉብኝት አስመልክቶ…

ለጤና ተቋማት መልሶ ግንባታ የሚውል የ31 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአውሮፓ ሕብረት በሰሜን ኢትዮጵያ  ግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት መልሶ ማቋቋሚያ የሚውል የ31 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አድርጓል፡፡ በአማራ፣ አፋር እና ትግራይ ክልሎች የሚገኙ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን 160 የጤና…

ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ለአፍሪካ የተቋም መሪዎች የሚሰጠውን ልዩ ሽልማት ለመቀበል ወደ እንግሊዝ አቀኑ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ  ቃበታ ለአፍሪካ የተቋም መሪዎች የሚሰጠውን ልዩ ሽልማት ለመቀበል ወደ እንግሊዝ አቀኑ፡፡ ሽልማቱን ያዘጋጀው ጠንካራ ተቋማት በመገንባት አርአያነት ያለው  ስራ ላከናወኑ መሪዎች ዓለም ዓቀፍዊ እውቅናና  ሽልማት…

በትግራይ ክልል በጦርነት ጉዳት ለደረሰበት ት/ቤት  ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣቶች በትግራይ ክልል እንደርታ ወረዳ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰበት ደብረ መድኃኒት ት/ቤት የግንባታ ግብዓት ድጋፍ አደረጉ፡፡ ከግንባታ ግብዓት ድጋፉ በተጨማሪም አረንጓዴ ዐሻራ የማኖር እና ለሕጻናት…

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሰዓሊ ጁሊ ምህረቱ አዲሱን የቢ ኤም ደብሊው መኪና እንድታስውብ ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአብስትራክት ስዕሎቿ የምትታወቀው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ጁሊ ምህረቱ አዲሱን የቢ ኤም ደብሊው መኪና በስዕል እንድታስውብ ተመርጣለች፡፡ ሰዓሊዋ የቢ ኤም ደብሊው የዲዛይን ፕሮጀክትን በሚመሩት የዓለም አቀፍ የሙዚየም ዳይሬክተሮች እና ተቆጣጣሪ ዳኞች…

200 ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ በካናሪ ደሴቶች መጥፋቷ ተሰማ  

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 200 ሰዎችን አሳፍራ ወደ ስፔን ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ ፍለጋ እንደቀጠለ መሆኑን የስፔን የነፍስ አድን ሰራተኞች አስታወቁ። ከደቡባዊ ሴኔጋል ተነስታ ወደ ካናሪ ደሴት እያመራች ነበር የተባለችው የአሳ ማጥመጃ ጀልባ ህጻናትን ጨምሮ 200…

በዱራሜ ከተማ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በከምባታ ጠምባሮ ዞን ዱራሜ ከተማ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች  ተመርቀዋል፡፡ ዛሬ ለምርቃ  የበቁት ፕሮጀክቶች የሕዝብ መድኃኒት ቤት፣ የእሳት አደጋ መከላከያ፣ ለወጣቶች የሚተላለፉ የንግድ ቤቶች፣ የከንባታ ማኅበረሰብ…