Fana: At a Speed of Life!

ጎሕ ቤቶች ባንክና የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጎሕ ቤቶች ባንክ ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡ ስምምነቱን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አስማረ እና የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ…

አቶ ዓለምአንተ አግደው ከኤፍ ቢ አይ ረዳት ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ አለምአንተ አግደው ከአሜሪካ የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ) ረዳት ዳይሬክተር ራይመንድ ዱዳ ጋር በሁለቱ ሀገራት የጋራ የሕግና የፍትሕ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡ በውይይታቸውም አቶ አለምአንተ አግደው በኢትየጵያ…

ሞዴል አዳሪ ትምህርት ቤቶች ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ስለሚኖራቸው ግንኙነት አሠራር ይዘረጋል- ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር በየአካባቢው የሚገኙ ሞዴል አዳሪ ትምህርት ቤቶች በአካባቢያቸው ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ሊኖራቸው ስለሚገባ ግንኙነት አሠራር እንደሚዘረጋ ተገለጸ፡፡ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ የጋሞ ባይራ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን…

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ልዩ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1ኛ ልዩ ጠቅላላ ጉባዔውን እያካሄደ ነው። በጉባዔው የክልል ተወካዮች እየተሳተፉ ሲሆን÷ የምክር ቤቱ የ100 ቀን እቅድ እና ክንውን ሪፖርት ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የ2015 በጀት ዓመት…

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት ማካሄድ ጀመሩ። በውይይቱ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር የስራ…

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በ2ኛ አመት 5ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በዚህም መሰረት ፥ የጥቁር ህዝቦች ነፃነትና የጀግንነት ማሳያ አርማ የሆነው የአድዋ ሙዚየም የኪነጥበብ ስራ ላይ ተወያይቶ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ተወክለው…

በርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የተመራ ልዑክ በአሶሳ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በአሶሳ ግብርና ምርምር ማዕከል የተሰሩ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል፡፡ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በግብርና ምርምር ማዕከሉ እየተከናወኑ…

አርቲስት አሊ ቢራ የትውልዶች ሁሉ ማስተማሪያ ነው -የሙዚቃ ባለሙያዎች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ የትውልዶች ሁሉ ማስተማሪያና በጥበብ ስራዎቹ ራሱን አስከብሮ የኖረ ነው ሲሉ የሙዚቃ ባለሙያዎች ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ የሙዚቀኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳዊት ይፍሩ፣ የሙዚቃ ባለሙያው ሰርጸፍሬ ስብሀትና ሌሎች…

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የህወሓት ታጣቂዎች አዛዦች ናይሮቢ ላይ ተገናኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የህወሓት ታጣቂዎች አዛዦች ናይሮቢ ላይ ተገናኙ። በሰላም ስምምነቱ ውስጥ በአምስት ቀን ውስጥ ወታደራዊ አመራሮች እንዲገናኙ በሚያዘው መሠረት የአዛዦቹ ውይይት ዛሬ በናይሮቢ ተጀምሯል ። እስካሁን የስምምነቱ ሂደቱ…

የሰላም ስምምነቱ  በሀገሪቱ ሰላምን ለማስፈንና ልማትን ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥል ነው-የሐረሪ ክልል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ስምምነቱ በሀገሪቱ ሰላምን ለማስፈንና ልማትን ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥል እና መንግስትና ህዝባችን ፊቱን ሙሉ በሙሉ ወደ ልማት እንዲያዞሩ እድል የሚፈጥር ነው ሲል የሐረሪ ክልል ገለፀ፡፡ በኢትዮጵያ መንግስትና በሕወሀት መካከል የተደረሰውን…