Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን ደቡብ አፍሪካን በማሸነፍ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን ደቡብ አፍሪካን 2 ለ 0 በማሸነፍ በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን አረጋገጠች። ሱዳን በሜዳዋ ባፋና ባፋናዎችን አስተናግዳ ከእረፍት በፊት በተቆጠሩ ሁለት ጎሎች ከ12 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ አልፋለች፡፡…

አዲስ አበባ ለሚገኙ ሲሚንቶ ፈላጊዎች 50 ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ ከ377 ብር በታች እንዲሸጥ ተወሰነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች አማካኝነት የቀረበ 50 ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ አዲስ አበባ ለሚገኙ ሲሚንቶ ፈላጊዎች ከ377 ብር በታች እንዲሸጥ መወሰኑን የንግድን ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በዚህም ደርባ 343 ብር ከ35፣ ሙገር 352 ብር…

የስዊዝ ቦይን ለአንድ ሳምንት ዘግታ የነበረችው መርከብ መንቀሳቀስ ጀመረች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ስዊዝ ቦይን ለአንድ ሳምንት ዘግታ የነበረችው ግዙፏ ዘ ኤቨር ጊቭን መርከብ መንቀሳቀስ መጀመሯ ተገለፀ። 400 ሜትር የምትረዝመው ግዙፍ እቃ ጫኚ መርከብን ከነበረችበት ሁኔታ 80 በመቶ መልኩ ተስተካክላ መንቀሳቀስ መጀመሯን ነው የስዊዝ ቦይ…

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያና የምርጫ ማኒፌስቶ ትውውቅ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር በባሕር ዳር ተካሄደ። በዚህ መድረክ የምርጫ ማኒፌስቶና የእጩዎች ትውውቅም ተካሂዷል። በስነ ስርዓቱ ላይም የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የብልጽግና…

የኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የዕውቅናና ምስጋና መርሀ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ለአፍሪካ ብሎም ለኢትዮጵያ በኦሎምፒክ መድረክ በ10 ሺህ ሜትር በባርሴሎና የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት ለሆነች ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የዕውቅናና ምስጋና መርሀ ግብር ተካሄደ። በስነ ስርዓቱ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣…

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አነሳ፡፡ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ከተማን 2-1 በማሸነፍ ዋንጫውን ሊያነሳ ችሏል። በሎዛ አበራ ሁለት ጎሎች…

የተሻለ ጥራት ያለው አገልግሎት ለሰጡ 10 የፌዴራል መንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ከኢፌድሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመሆን የመንግስት አገልግሎት ጥራት ላይ ያዘጋጀው ልዩ ውድድር ማጠቃለያ ፕሮግራም ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ 10 የፌዴራል መንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የአገልግሎት…

በጋምቤላ ክልል በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ተጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጋምቤላ ክልል ያለውን ሰላም በማጠናከር የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ የክልሉ ምክር ቤት ጠየቀ። የክልሉ ምክር ቤት ስድስተኛ የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ…

ከ5 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት “ደብሊውኤ የዘይት ፋብሪካ” የሙከራ ምርት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደብረማርቆስ ከተማ ከ5 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት እና በባለሃብቱ አቶ ወርቁ አይተነው የተገነባው "ደብሊውኤ የዘይት ፋብሪካ" የሙከራ ምርቱን ዛሬ ጀምሯል። የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገርና ሌሎች የክልልና የዞን…

ከከተማ እስከ ወረዳ የሚገኙ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክትን  ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከከተማ እስከ ወረዳ የሚገኙ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መለሠ…