Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር አሰልጣኝ ፍራንክ ናፓልን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከደቡብ አፍሪካዊው አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ ጋር በስምምነት የተለያየው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር  አሰልጣኝ ፍራንክ ናፓልን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡ አሰልጣኝ ፍራንክ በእግር ኳሱ ዘርፍ ከ35 ዓመታት በላይ በተለይ በአፍሪካ በማሰልጠን…

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጅማ ዞን ሰቃ ወረዳ በበጋ መስኖ የለማን የስንዴ ማሳ ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጅማ ዞን ሰቃ ወረዳ በበጋ መስኖ የለማን የስንዴ ማሳ ጎበኙ፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በወረዳው በበጋ መስኖ በኩታ ገጠም የለማውን የስንዴ ምርት እየተሰበሰበ ያለበትን ሂደት ተመልክተዋል።…

299 ዜጎች ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 299 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ጂዳ ከተማ ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የውጭ…

ኦ የደም አይነት እጥረት ማጋጠሙን ብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት በኦ የደም አይነት እጥረት እንዳጋጠመው አስታወቀ። አገልግሎቱ አሁን ላይ በክምችቱ የሚገኘው ኦ የደም አይነት ለሰባት ቀናት ብቻ መሆኑን ነው የገለፀው። በመሆኑም ኦ የደም አይነት ያላቸው ዜጎች…

የምርምር ስራዎች የምርምር ስነምግባር መርሆዎችን ተከትለው እንዲሠሩ የሚያስችል ስልጠናዊ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምርምር ስራዎች የምርምር ስነምግባር መርሆዎችን ተከትለው እንዲሠሩ በተቋማት የሚገኙ የምርምር ስነምግባር ኮሚቴዎችን አቅም መገንባትና ማጠናከር የሚያስችል ስልጠናዊ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ ስልጠናው ከፍተኛ የትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ…

ጠ/ሚ ዐቢይ ለዋልያዎቹ መልካም ውጤት ተመኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኢትዮጵያ የወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) መልካም ውጤት ተመኙ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ዕድሉን አስፍቷል ሲሉ አስፍረዋል።…

በደቡብ ክልል ባስኬቶ ልዩ ወረዳ የእርስ በርስ ግጭት በማስነሳት ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ ከ35 በላይ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ባስኬቶ ልዩ ወረዳ በ11 ቀበሌ የእርስ በእርስ ግጭት በማስነሳት ለአራት ሰዎች ህይወት መጥፋትና 31 ሺህ ሰዎች ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ አድርገዋል  የተባሉ ከ35 በላይ ተከሳሾች  ከ8ስምንት እስከ 20 አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ተቀጡ።…

የስዊዝ ካናል መዘጋት በየቀኑ 9 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ባለው ሸቀጥ ግብይት ላይ መስተጓጎል ፈጥሯል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የስዊዝ ካናል በአንድ ግዙፍ መርከብ በመዘጋቱ በየቀኑ 9 ቢሊየን ዶላር የሚገመት የሸቀጥ ግብይት ላይ መስተጓጎል እየተፈጠረ መሆኑ ተነግሯል። ለምስራቁና ምዕራቡ ዓለም ወሳኝ በሆነው በዚህ የውሃ መተላለፊያ መስመር በሰዓት 400 ሚሊየን ዶላር ዋጋ…

በደቡብ ክልል ማር ለመቁረጥና የእርሻ መሬትን ለማስፋፋት በሚደረግ እንቅስቃሴ በደን ሀብቶች ላይ ውድመት እየደረሰ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ማር ለመቁረጥ፣ የእርሻ መሬትን ለማስፋፋት፣ ከሰል ለማክሰልና አዲስ የመኖ ሳር ለማብቀል በሚደረግ እንቅስቃሴ በደን ሀብቶች ላይ ውድመት እየደረሰ መሆኑን የክልሉ የአካባቢ ጥበቃ፣ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ባለስልጣን…

እነ አቶ ስብሃት ነጋ ያቀረቡት ዳኛው ከመዝገባችን ይነሳ ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እነ አቶ ስብሃት ነጋ ያቀረቡት ዳኛው ከመዝገባችን ይነሳ ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ባሳለፍነው ሳምንት የጊዜ ቀጠሮ ጉዳያቸውን የተመለከቱት ዳኛ ገለልተኛ ሆነው ስለማይመለከቱልን ከመዝገቡ ይነሱልን ሲሉ ማመልከታቸው ይታወሳል፡፡…