Fana: At a Speed of Life!

በ2011 ዓ.ም በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የደረሰው አደጋ የመጨረሻ ሪፖርት በቅርቡ ይፋ ይሆናል- ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2011 ዓ.ም በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የደረሰው አደጋ የመጨረሻ ሪፖርት በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ…

ተጨማሪ 300 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረብያ ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት ተጨማሪ 300 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረብያ ጂዳ ከተማ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይረክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገዉላቸዋል።…

የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ የኢንዱስትሪ ፓርክ የመጀመሪያ ምዕራፍ በመጭው ቅዳሜ ይመረቃል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ የኢንዱስትሪ ፓርክ የመጀመሪያ ምዕራፍ በመጭው ቅዳሜ ይመረቃል፡፡ በ294 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ፓርኩ 152 ሺህ ሼዶች ይኖሩታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ፓርኩ የአቮካዶ ዘይት፣ የአቮካዶ ማር፣ ቡደና…

ለህዝብ የቀረቡ ፖሊሲና ስትራቴጅዎች ማዘጋጀታቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለህዝብ የቀረቡ ፖሊሲና ስትራቴጅዎችን ማዘጋጀታቸውን ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ በማህበራዊ እና ምጣኔ ሃብት ፍትሃዊነት ላይ ትኩረት ያደረገ ፖሊሲና ስትራቴጅ…

በፕሪሚየር ሊጉ ባህርዳር ከተማ አዳማ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህር ዳር ከተማ አዳማ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል። በጨዋታው ፍፁም አለሙ ለቡድኑ ብቸኛዋንና የማሸነፊያ ግብ በ22ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል። በዚህ ባህርዳር ከተማዎች ደረጃቸውን በማሻሻል ሶስተኛ ላይ…

ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ ‘ሆፕ ፎር ፋዘርለስ’ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ 'ሆፕ ፎር ፋዘርለስ' የተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅትን ጎበኙ። በ2008 ዓ.ም የተቋቋመው 'ሆፕ ፎር ፋዘርለስ' የተሰኘው አገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት ወላጅ አልባና ድጋፍ የሚሹ ህጻናትን ለመደገፍ የተቋቋመ  መሆኑን…

40 የሩሲያ የጎብኚዎች ቡድን የኢትዮጵያን እሴቶችና የመስህብ ስፍራዎች ለማስተዋወቅ ያለመ ጉብኝት እያደረገ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 40 ሩሲያውያንን ያቀፈ የሩሲያ የጎብኚዎች ቡድን በኢትዮጵያ የተለያዩ ስፍራዎችን እየጎበኘ ነው፡፡ የቡድኑ ጉብኝት ኢትዮጵያ ያላትን ታሪካዊ፣ የተፈጥሮ እና ባህላዊ እሴቶችን ለቀሪው ዓለም ለማስተዋወቅ ያለመ ነው ተብሏል፡፡ የናሽናል ጂኦግራፊ…

የትግራይ ሕዝብ ሀገር ያጸና፣ ለሀገር መስዋዕትነት የከፈለ ነው፤ ይህን የሚገፋ አካል ካለ ‘ታሪክ ያበላሻል’ -ዶ/ር አብርሃም

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የራሳቸውን ፍላጎት ለሟሟላት ለሚሯሯጡ ቡድኖች ተብሎ የሚፈርስ ሀገር የለም ሲሉ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ገለፁ። ሚኒስትሩ የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያን ከገነቡ ሕዝቦች አንዱ መሆኑንም ነው የገለጹት። ይሁንና የሕዝብ…

ቀይ መስቀል በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍና ለሆስፒታሎች ምግብ እና የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል የህግ ማስከበር እርምጃውን ተከትሎ ለተፈናቀሉ  ዜጎች ድጋፍ አድርጓል። በመቀሌ፣ አብዱራፊ፣ አዲግራት እና ሽሬ ለሚገኙ 9 ሺህ 125 አባወራዎች…

አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ከፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስቴር ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ሃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ከፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስቴር ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ሃላፊ ሜጀር ጄኔራል ሎረን ማርበፍ ጋር ተወያዩ፡፡ በወቅቱም በሁለቱ ሃገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አምባሳደር ሄኖክ አስታውቀዋል፡፡…