Fana: At a Speed of Life!

ከአዲስ ቅዳም ወደ እንጅባራ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሽ ተገልብጦ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአዲስ ቅዳም ወደ እንጅባራ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሽ ተገልብጦ በስምንት ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደረሰ፡፡ አደጋው በተለምዶ አድጓሚ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ተሽከርካሪ በመገልበጡ የደረሰ መሆኑን የአዊ ዞን ኮሙዩኒኬሽን መረጃ…

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአንካራ የተገነባውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱርክ አንካራ የተገነባው አዲሱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዛሬው እለት ተመርቋል። በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቩሉት ካቩሶግሉ ተገኝተዋል።…

ሰማሪታንስ ፐርስ በትግራይ ድጋፍ ለሚሹ ወገኞች ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ዓልሚ ምግብ አበረከተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰማሪታንስ ፐርስ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በትግራይ ክልል ሠብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ዓልሚ ምግብ ድጋፍ አደረገ፡፡ ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤቱ ከሚገኝበት ሰሜን ካሮላይና ግዛት ቡን…

25 የገጠር ከተሞችን ከፀሃይ ሃይል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 25 የገጠር ከተሞችን ከፀሃይ ሃይል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ። በስምምነት መድረኩ ላይ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡…

ጊኒ የኢቦላ ወረርሽኝ መከሰቱን ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጊኒ በኢቦላ ወረርሽኝ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ ቫይረሱ በወረርሽኝ ደረጃ መከሰቱን ይፋ አደረገች። በጊኒ ደቡብ ምስራቅ በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ለህልፈት ከተዳረጉት ሰዎች ባሻገር አራት ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተነግሯል።…

አትሌት ጌትነት ዋለ እና አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በፈረንሳይ የቤት ውስጥ ውድድር አሸናፊ ሆነዋል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጌትነት ዋለ እና አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በፈረንሳይ በተካሄደ የቤት ውስጥ ውድድር አሸናፊ ሆነዋል፡፡ አትሌት ጌትነት ዋለ በ1 ሺህ 500 ሜትር መሰናክል ውድድር 3 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ ከ54 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሸናፊ…

የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ የፓርቲውን ማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ይፋ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) "ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለጋራ ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል የምርጫ 2013 የብልጽግና ፓርቲ ማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ይፋዊ የእውቅና መድረክ በሸራተን አዲስ ተካሂዷል፡፡ የዕውቅና መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ የከፈቱት…

ሶስት የልማት ድርጅቶች ባለፉት ስድስት ወራት ከ200 ሚሊየን በላይ አተረፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በማምረቻና ኢነርጂ ዘርፍ የተሰማሩ ሶስት የልማት ድርጅቶች በመጀመሪያው አጋማሽ ዓመት ከ200 ሚሊየን ብር በላይ አተረፉ። በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ሥር ካሉት የልማት ድርጅቶች መካከል ሶስት የልማት ድርጅቶች ባለፉት…

በ24 ሰዓት ውስጥ አራት ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገንዘብ አባዝተን እንሠጣለን በማለት ሲያጭበረብሩ የነበሩ ሁለት ካሜሮናውያንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ…

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር በ24 ሰዓት ውስጥ አራት ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገንዘብ አባዝተን እንሠጣለን በማለት ሲያጭበረብሩ የነበሩ ሁለት ካሜሮናውያንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ፡፡…

ባይደን በሜክሲኮ የሚገኙ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች ወደ አሜሪካ እንዲገቡ ሊፈቅዱ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በሜክሲኮ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞችን ወደ አሜሪካ እንዲገቡ ሊፈቅድ ነው፡፡ የአዲሱ ፕሬዚዳንት አስተዳደር በሜክሲኮ የሚገኙ ስደተኞችን ጉዳይ በማየት ወደ አሜሪካ የማስገባት ሂደት…