Fana: At a Speed of Life!

የሕወሓት ጁንታ የትግራይ መሠረተ ልማቶችን እያፈረሰ ነው – አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕወሓት ጁንታ የትግራይ መሠረተ ልማቶችን እያፈረሰ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ። የመከላከያ ሠራዊት ወደፊት መገሥገሡ ያስጨነቀው ጁንታ፣ በሁሉም አቅጣጫ ወደ መቐለ በሚወስዱት መንገዶች ላይ የሚገኙ አራት ድልድዮች…

በ24 ሰዓታት 339 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 3 ሺህ 778 የላብራቶሪ ምርመራ 339 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 103 ሺህ 395 መድረሱንም ሚኒስቴሩ…

ጠ/ሚ ዐቢይ “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብርን ላዘጋጁና ለተሳተፉ ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብርን ላዘጋጁና ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋና አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ፥ “በሀገሬ ሕዝብና በኢትዮጵያዊነቴ ኮራሁ” ብለዋል።…

“የኢትዮጵያ መንግሥት ከደቡብ ሱዳን የጦር ድጋፍ እንዲደረግለት በደብዳቤ ጠይቋል ተብሎ የሀሰት ዜና ተሰራጭቷል­- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ…

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) "የኢትዮጵያ መንግሥት ከደቡብ ሱዳን የጦር ድጋፍ እንዲደረግለት በደብዳቤ ጠይቋል" ተብሎ የሀሰት ዜና መሰራጨቱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ገለፀ። እንዲህ ያሉ የፈጠራ ዜናዎች፣ የሀገር ውስጥ ጉዳይን ቀጣናዊ ገጽታ ያለው አስመስሎ ለዓለም…

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ በምሥራቅና በምዕራብ ግንባሮች ወሳኝ ድሎችን መቀዳጀቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዛሬ ኅዳር 8 የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ በምሥራቅና በምዕራብ ግንባሮች ወሳኝ ድሎችን ተቀዳጅቷል። በምሥራቁ ግንባር ራያ ሙሉ በሙሉ ነጻ ወጥቷል፤ ጨርጨር፣ ጉጉፍቶ መሖኒን ሠራዊቱ ነጻ አውጥቷል። በየቦታው የነበሩ ወሳኝ የኮንክሪት ምሽጐችንም…

ዋልያዎቹ የኒጀር አቻቸውን 3ለ0 አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) የኒጀር አቻቸውን 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል። የኢትዮጵያ የወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታቸውን ዛሬ ከኒጀር ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም አካሂዷል።…