Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በገበታ ለሀገር አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 13 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በገበታ ለሀገር ተሳትፈው ዐሻራቸውን እንዲያሳርፉ ጥሪ አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ የዛሬ ዓመት ቃል የገባነውን ፈጽመን በተግባር አሳይተናል…

ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በተጠረጠሩበት ወንጀል ዐቃቤ ህግ በ10 ቀን ውስጥ ክስ እንዲመሰርት ብይን ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 13 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በተጠረጠሩበት ሁከትና አመጽ በማስነሳት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ ወንጀል አቃቤ ህግ በ10 ቀን ውስጥ ክስ እንዲመሰርት ብይን ተሰጠ፡፡ መርማሪ ፖሊስ በኢኒጂነር ይልቃል ላይ ሲያከናውን የነበረውን ምርመራ…

የሰላም ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የዕርቀ ሰላም ኮሚሽን በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡ ስምምነቱ በአቅም ግንባታ፣ በሀብት አጠቃቀም፣ በመረጃ ልውውጥ፣ በልምድ ልውውጥ እና ተዛማጅነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል…

ጆ ባይደን ዴሞክራቶችን በመወከል የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተፎካካሪ ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጭው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጆ ባይደን ዴሞክራቶችን በመወከል የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተፎካካሪ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ባይደን ፓርቲው ባካሄደው ታላቅ ጉባኤ ላይ በተካሄደው ምርጫ በይፋ የፓርቲው ተወካይ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡…

32 የኦነግ ሸኔ አባላት ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው እጃቸውን ለመንግስት ሰጡ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 13 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 32 የኦነግ ሸኔ አባላት ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ እጃቸውን ለመንግስት ሰጡ፡፡ አባላቱ ኦሮሞን ነጻ እናውጣ በሚል ሽፋን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን የመግደል፣…

ሚኒስቴሩ በተጠናቀቀው በጀት አመት 233 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር በተጠናቀቀው በጀት አመት 233 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ገለፀ። ሚኒስቴሩ በበጀት አመቱ 270 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ የእቅዱን 86 በመቶ ማሳካቱን አስታውቋል። ከዚህ ውስጥ 128 ነጥብ 7 ቢሊየን…

የደብረ ታቦር በዓል( ቡሄ) በደብረ ታቦር ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 13 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደብረ ታቦር በዓል( ቡሄ) በደብረ ታቦር ከተማ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ይገኛል። በዓሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አማንያን ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ በታቦር ተራራ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትን በማሰብ በየአመቱ ነሃሴ 13…

የማሊው ፕሬዚዳንት ቡባካር ኪዬታ በወታደሮች በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ስልጣን መልቀቃቸውን ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 13 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የማሊው ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኬዬታ በትናንትናው ዕለት በሀገሪቱ ወታደሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ፕሬዚዳንቱ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በሀገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ባስተላፉት መልዕከት ስልጣን መልቀቃቸውን በመግለፅ ፓርላማው መበተኑን…

“ደብረታቦርን በደብረታቦር” በሚል የቡሄ በዓል ለ3ኛ ጊዜ በደብረታቦር ከተማ ይከበራል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደብረታቦር /ቡሄ/ በዓል ህዝባዊ ባህሉን፣ የቀደመ የአከባበር ታሪኩን በጠበቀ እና በተለየ መልኩ በደብረታቦር ከተማ እንዲከበር በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ። በነገው እለት የሚከበረውን የደብረታቦር /ቡሄ/ በዓል አስመልክቶ…

በ24 ሰዓታት 1 ሺህ 386 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ28 ሰዎች ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 22 ሺህ 101 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 386 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 32 ሺህ 722…