Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል አሌ ልዩ ወረዳ በደረሰ የመሬት ናዳ የ12 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል አሌ ልዩ ወረዳ ጎሮዜ ቀበሌ ትናንት በተከሰተ የመሬት ናዳ የ12 ሰዎች ህይወት አለፈ። ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች መካከልም እስካሁን የ5 ሰዎች አስከሬን መገኘቱ ነው የተገለፀው። የመሬት ናዳው በስድስት የመኖሪያ ቤቶች ከእነ…

ጠ/ሚ ዐቢይ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር በስልክ ተወያዩ። በውይይታቸው የኮቪድ19 ወረርሽኝን መከላከል በሚቻልባቸው አግባቦች ዙሪያ መምከራቸውን በፌስ ቡክ ገጻቸው አስታውቀዋል። ጠቅላይ…

በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ፓርቲዎች ከምርጫ ጋር ተያይዞ እየተነሱ ላሉ ችግሮች ኢ-ህገመንግስታዊ መፍትሔዎችን እንደማይቀበሉ ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፓርቲ ወይም ከቡድን ፍላጎት በመውጣት የሀገሪቱን ችግሮች ለመቅረፍ እና ሀገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን አስታወቁ። የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ)፣…

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከኢስቶኒያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋችው ከኢስቶኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኡርማስ ሬይንሳሉ ጋር ተወያዩ። በውይይታቸውም የሃገራቱን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች እና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በትብብር መከላከል…

በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በአፍሪካ እስከ 190 ሺህ ሰዎች በመጀመሪያው ዓመት ህይዎታቸው ሊያልፍ ይችላል – የዓለም ጤና ድርጅት

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ከ83 ሺህ እስከ 190 ሺህ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በመጀመሪያው ዓመት ብቻ ህይዎታቸው ሊያልፍ እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ። ድርጅቱ ትናንት ባወጣው መግለጫ በአፍሪካ ሃገራት ቫይረሱን ለመከላከል የወጡ መመሪያና…

ኮሚሽኑ ተቋማት የኮቪድ19 ወረርሽኝን ከመከላከል ጎን ለጎን ሙስናን መከላከል ላይ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳሰበ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ከመከላከል ጎን ለጎን ተያይዘው የሚመጡ የሙስና ተግባራትን መከላከል ላይ ሊዘናጉ እንደማይገባ የፌደራል ጸረ ሙስና ኮሚሽን አሳሰበ። መንግስት ህዝቡን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተከሰተው…

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 194 ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ለ1 ሺህ 861 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሶስት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው አስታወቀ። ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሴቶች ሲሆኑ፥ እድሜያቸው ከ23 እስከ 33 አመት…

አቶ በረከት ስሞኦን የስድስት እንዲሁም አቶ ታደሰ ካሳ የስምንት አመት እስራት ተወሰነባቸው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአቶ በረከት ስሞኦን የስድስት እንዲሁም በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ ደግሞ የስምንት ዓመት የእስር ፍርድ ወሰነ። ፍርድ ቤቱ ሚያዚያ 28 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት ዓቃቤ ህግ ያቀረባቸውን የቅጣት ማክበጃ እና…

ጠ/ሚ ዐቢይ በመስኖ ልማት የስንዴ ምርታማነትን ለመጨመር መታቀዱን አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስንዴን ከውጭ በማስገባት ፈንታ በመስኖ በማልማት ምርታማነት ለመጨመር መታቀዱን አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛውን የስንዴ መጠን ለማምረት ከሚችሉ ሀገራት መካከል መሆኗን…

በአማራ ክልል ከውጭ ሀገራት በየብስና በትራንዚት ወደ ክልሉ የሚገቡ የውጭ ተመላሾች  ለኮቪድ-19 መስፋፋት ስጋት መሆናቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 30 ፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የኮቪድ-19 መከላከልና መቆጣጠር ስራ ከውጭ ሀገራት በየብስና በትራንዚት ወደ ክልሉ የሚገቡት የውጭ ተመላሾች  ስጋት መሆናቸው ተገለፀ። በአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽና መልሶ ማቋቋም ባለሙያ አቶ ሀይሉ አያሌው…