Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ላይ ያላትን አቋም ለማስረዳት ወደተለያዩ የዓለም ሀገራት ልኡካን ቡድኖችን ላከች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴው ግድብ ላይ ያላትን አቋም ለማስረዳት ወደተለያዩ የዓለም ሀገራት ከፍተኛ የልኡካን ቡድኖችን በመላክ ላይ ትገኛለች። በዚሁ መሰረት በኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የተመራ ከፍተኛ የአገራችን የልኡካን ቡድን በዛሬው…

በምስራቅ ሸዋ ዞን ለወንጀል ድርጊቶች ማስፈፀሚያ ሲውሉ የነበሩ 377 ሞተር ሳይክሎች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሸዋ ዞን 7 ወረዳዎች በተካሔደ ድንገተኛ ፍተሻ ለተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ማስፈፀሚያ ሲውሉ የነበሩ 377 ሞተር ሳይክሎች መያዙን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ። የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ…

በግብርና ሚኒስቴር የመጀመሪያ ደረጃ የካይዘን ትግበራ መርሃ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2012  (ኤፍ ቢ ሲ)በግብርና ሚኒስቴር የመጀመሪያ ደረጃ የካይዘን ትግበራ መርሃ ግብር ይፋ ተደረጓል። መርሃ ግብሩ “ካይዘን ለተቋማዊ ትራንስፎርሜሽን” በሚል መሪ ቃል የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ይፋ  መሆኑን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ…

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በናይሮቢ ተገናኝተው ተወያይተዋል። የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የስራ ጉብኝት ለማድረግ በዛሬው እለት ኬንያ ናይሮቢ ገብተዋል። በቆይታቸውም ፕሬዚዳንት…

ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አገር መከላከያ ምክትል የኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጋር ተወያዩ። በጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የተመራ የልዑካን ቡድን በሱዳን የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ መሆኑን በሱዳን የኢትዮጵያ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሁለት ሹመቶችን ሰጡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሁለት ሹመቶችን ሰጥተዋል። በዚህ መሰረትም ፦ 1.ወይዘሮ ህይወት ሞሲሳ- የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር እና 2.ሜጀር ጀኔራል አህመድ ሀምዛ - የመከላከያ…

ሰራዊቱ የሀገሪቱን ሰላምና ሉዓላዊነት የማስከበር ተልዕኮውን ለመወጣት በላቀ ብቃት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የሚቃጣ ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት እና አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ። የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ጀኔራል አደም መሃመድ፣ የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ሜጀር…

ለቀናት ሲካሄድ የነበረው የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ መካከለኛ አመራሮች ስልጠና በስኬት መጠናቀቁን የክልሉ የፓርቲው ፅህፈት ቤት ገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለ15 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ መካከለኛ አመራሮች ስልጠና በስኬት መጠናቀቁን የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ገለፁ። የስልጠናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ አቶ ፍቃዱ መግለጫ ሰጥተዋል።…

ከመጋቢት 10 ጀምሮ አዲስ ፓስፖርት በ1 ወር ጊዜ ውስጥ መሰጠት ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ከመጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ፓስፖርት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መስጠት ሊጀምር መሆኑን ገለጸ።   የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጅብ ጀማል እንደገለጹት፥ ከዚህ…

የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር እና የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀገሪቱ የሚስተዋለውን የትራፊክ አደጋ ለመቆጣጠር የግንዛቤ ፈጠራና የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል። የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ያደታ በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥…