Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ክልል መንግስት ለ2 ሺህ 332 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 2 ሺህ 332 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል። የቢሮው ሃላፊ አቶ ተኪኡ ምትኩ በሰጡት መግለጫ፥ የክልሉ መንግስት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)…

የቱኒዚያ አዲሱ መንግስት የመተማመኛ ድምጽ አገኘ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱኒዚያ አዲሱ መንግስት በፓርላማው የመተማመኛ ድምጽ አገኘ። ፓርላማው ባለፈው ወር ማብቂያ ላይ በሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ካይስ ሳይድ የቀረበውን የኤልዬስ ፋክህፋክህን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመትም አጽድቆታል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመሰረተው…

በመዲናዋ ዘመናዊ የትራፊክ ቁጥጥር ስርዓት ተግባራዊ ሊደረግ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ማሳለጥ የሚያስችል የኢንተለጀንት ትራፊክ ቁጥጥር ስርዓት ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ። ስርዓቱ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ እንደሚደረግ የከተማዋ ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታውቋል።…

ቦርዱ ከተለያዩ የአካል ጉዳተኛ ማህበራት ጋር ምክክር እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተለያዩ የአካል ጉዳተኛ ማህበራት ጋር ምክክር እያደረገ ነው። ቦርዱ አካል ጉዳተኞች በምርጫ ሂደት ስላላቸው ተሳትፎ እንዲሁም በአዲሱ የምርጫ ህግ አካታችነት ዙሪያ ነው ውይይቱን እያደረገ ያለው።…

ሳዑዲ ዓረቢያ ወደ መካ የሚደረጉ ጉዞዎችን አገደች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳዑዲ ዓረቢያ ወደ መካ የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ እገዳ መጣሏን አስታወቀች። የጉዞ እገዳው ሐይማኖታዊ እና መደበኛ ተጓዦችን የሚያካትት ሲሆን፥ የስርጭት አድማሱን እያሰፋ ካለው የኮሮና ቫይረስ ጋር የተያያዘ መሆኑንም አስታውቃለች። ይህን…

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ሰባት ወራት 24 ቢሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ሰባት ወራት 24 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አስታውቋል። ቢሮው በቀጣይ በሚያደርገው የገቢ ማሻሻያ የታክስ ንቅናቄ መሪ እቅድ ዙሪያ ከሚመለከታችው የመንግስት አካላትና የንግዱ ማህበረሰብ…

አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ በኮሮና ቫይረስ ስጋት ዓመታዊ የጋራ ወታደራዊ ልምምዳቸውን አራዘሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት በየዓመቱ የሚያካሂዱትን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ አራዝመዋል። ዋሽንግተን እና ሴኡል ዓመታዊ የጋራ ወታደራዊ ልምምዳቸውን ያራዘሙት በሀገራቱ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ…

ኢትዮ ቴሌኮም በብሮድባንድ ኢንተርኔት አግልግሎቱ ላይ የዋጋ ቅናሽ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በብሮድባንድ ኢንተርኔት አግልግሎቱ ላይ ማሻሻያ እና የዋጋ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል። በዚህም ለግል ተጠቃሚዎች እስከ 69 በመቶ፣ ለVPN አግልግሎት እስከ 72 በመቶ እንዲሁም ለኢንተርፕራይዞች እስከ 65 በመቶ የሚደርስ…

የእንቅልፍ እጥረት እና ያልተስተካከለ አመጋገብ ሴቶችን ለልብ የጤና ችግር ያጋልጣል – ጥናት

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንቅልፍ እጥረትና ያልተስተካከለ የአመጋገብ ስርዓት ሴቶችን ከልብ ጋር ተያይዞ ለሚመጣ ችግር እንደሚያጋልጣቸው አንድ ጥናት አመላከተ። በአሜሪካ የተደረገውና ከሰሞኑ ይፋ የሆነው ጥናት የእንቅልፍ እጥረትና ያልተስተካከለ የአመጋገብ ስርአት…

ሶማሊያ የ330 ሚሊየን ዶላር እዳ ስረዛ ተደረገላት

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ለሶማሊያ የ330 ሚሊየን ዶላር እዳ ስረዛ መደረጉን አስታወቀ። እንደ ተቋሙ ገለጻ 100 አበዳሪዎች ለምስራቅ አፍሪካዊቷ ሃገር የዕዳ ስረዛውን ለማድረግ ተስማምተዋል። የዕዳ ስረዛው ሶማሊያ…