Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ ከ43 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸውን ቁሳቁሶች ለሜቄዶኒያ አበረከተ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ከ43 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ቁሳቁሶችን ለሜቄዶኒያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል አበረከተ፡፡ ድጋፉ የምግብ፣ የንጽህና መጠበቂያና አልባሳትን ያካተተ መሆኑን ማዕከሉ ለጣቢያችን የላከው መግለጫ…

ባለፉት 11 ወራት ከ259 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰብ ተችሏል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 11 ወራት ውስጥ 259 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው ገለጹ። በ2ዐ13 የበጀት ዓመት ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ ባሉት 11 ወራት ውስጥ ለመሰብሰብ ከታቀደው 264 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር 259 ነጥብ…

የኢትዮጵያ የብስክሌት ሻምፒዮና ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ያዘጋጀው የ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና በሞጆ ከተማ ተጀምሯል ። በውድድሩ ከአምስት ክልሎችና ከሁለት ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ70 በላይ ስፖርተኞች ተሳትፈዋል ። ዛሬ በመክፈቻው…

ኢትዮ ቴሌኮም በእንጦጦ ፓርክ ስማርት ማማ አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊ በሆነ መንገድ የገነባቸውንና ጎብኚዎች በእንጦጦ ፓርክ የኢንተርኔት ዳታ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸውን የስማርት ማማ አስመረቀ፡፡ ማማው የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች…

በአውሮፓ ዋንጫ ዌልስ እና ስዊዘርላንድ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ ዛሬ አንድ ጨዋታ አስተናግዷል፡፡ በአዘርባጃን ባኩ ከተማ የተካሄደው ጨዋታ በምድብ 1 የተደለደሉት ዌልስ እና ስዊዘርላንድን አገናኝቷል፡፡ ጨዋታው አንድ አቻ ሲጠናቀቅ ሙር ለዌልስ እንዲሁም ኢምቦሎ ለስዊዘርላንድ ጎሎቹን…

ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማህበር 3 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማህበር 3 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ሰጠ። ማህበሩ ሽሮ ሜዳ ቁስቋም አካባቢ 3 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ከከተማ አስተዳደሩ በነጻ የተረከበ ሲሆን በስፍራው ለሚገነባው የህሙማን ማገገሚያ…

በቦሌ ክፍለ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ 46 አባወራዎች የቤት ባለቤት ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቦሌ ክፍለ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ 46 አባወራዎች የተገነቡ ቤቶችን መርቀው አስረከቡ። ቤቶቹ በ18 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ ሲሆን ለነዋሪዎቹም የብርድ…

ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከጠ/ሚ ዐቢይ የተላከ ደብዳቤን ለፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት አደረሱ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከ ደብዳቤን ለፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አደረሱ፡፡ በሚኒስትሯ የተመራ ልዑክ ደብዳቤውን ለፕሬዚዳንቱ የአፍሪካ ጉዳዮች ልዩ አማካሪ ፍራንክ ፓሪስ…

ደብረብርሃንን አማራጭ የኢንዱስትሪ ከተማ ለማድረግ እየተሰራ ነው – አቶ አገኘሁ ተሻገር

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደብረብርሃን የሃገሪቱ አማራጭ የኢንዱስትሪ ከተማ እድትሆን የክልሉ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ ። ርዕሰ መስተዳድሩ ዛሬ በደብረብርሃን ከተማ ባለፉት 3 አመታት ተገንብተው ወደምርት…

በመዲናዋ በነገው እለት በፕሮጀክት ምረቃ ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል አደባባይ እና እስከ ማዘጋጃ ቤት የተከናወነው የመንገድ ግንባታ ምረቃ ምክንያት በማድረግ በነገው እለት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የመስቀል አደባባይ ግንባታ እና ከመስቀል…