Fana: At a Speed of Life!

ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ በ19 የህወሓት አመራርና አባላት ላይ እገዳ ተጣለ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ በ19 የህወሓት አመራርና አባላት በአዲስ አበባ የሚገኙ ቋሚ ንብረቶቻቸው ላይ እገዳ መጣሉን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ሃይል አስታወቀ፡፡ ግብረ ሃይሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ…

ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ማጠናከር አላማው ያደረገ የኢትዮ ቻይና ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ቻይና ኢኮኖሚያዊ ትብብር ማጠናከርን አላማው ያደረገ ምክክር በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ አካሄዱ፡፡ ምክክሩ በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛሆ ዢያን እንዲሁም ሌሎች የስራ ሃላፊዎች…

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከቻይና አምባሳደር ማ ዚንሚንጋር በወቅታዊ ሃገራዊና ቀጠናው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ በዚህ ወቅት አምባሳደር ይበልጣል በትግራይ ክልል ያለውን…

ቻይና የሁለት ልጅ ፖሊሲዋን ልታነሳ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በቤተሰብ ምጣኔ ላይ ትተገብረው የነበረውን የሁለት ልጅ ፖሊሲ ልታሻሽል ነው፡፡ የመንግስት ባለስልጣናትን ዋቢ ያደረገው የሺንዋ ዘገባ መንግስት ጥንዶች ሶስት ልጆችን እንዲወልዱ ሊፈቅድ መሆኑን ያመላክታል፡፡ መንግስት ከዚህ በፊት…

በምርጫ ወቅት ፓርቲዎች ሊያከብሯቸው የሚገቡ የሰብአዊ መብት አጀንዳዎች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊያከብሯቸው የሚገቡ ባለ ስድስት ነጥብ የሰብአዊ መብቶች አጀንዳ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች አቅርቧል። ፓርቲዎቹ እንዲያከብሯቸው የተቀመጡት የሰብአዊ መብቶች አጀንዳዎች፥…

የአውሮፓ ህብረት ፋኦ በኢትዮጵያ የበረሃ አንበጣን ለመከላከል ለሚያደርገው ጥረት 4 ነጥብ 1 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት ዓለም አቀፉ የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) በኢትዮጵያ የበረሃ አንበጣን ለመከላከል ለሚያደርገው ጥረት 4 ነጥብ 1 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገ፡፡ በህብረቱ የተደረገው ድጋፍ በአውሮፓ የህዝብ ጥበቃ እና ሰብአዊ እርዳታ ዘመቻ…

አቶ እርስቱ ይርዳ እና አቶ ሽመልስ አብዲሳ በእነሞር እና ኤነር ወረዳ ለሚገነባው ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ አኖሩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጉራጌ ዞን እነሞር እና ኤነር ወረዳ የጉስባጃይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ አኖሩ፡፡ በጉራጌ ዞን እነሞር…

“ድምፃችን ለነፃነታችን” በሚል በመላ ሀገሪቱ ሰላማዊ ሠልፍ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “ድምፃችን ለነፃነታችን” በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገሪቱ ወጣቶችን ያሳተፈ ሰልፍ ነገ እንደሚካሄድ ተገለፀ። ሰልፉ የውጭ ሀገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና የሚያሳድሩትን ጫና በመቃወም የሚከናወን ነው ተብሏል።…

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 122 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያስተማራቸውን 122 የህክምና ዶክተሮች አስመረቀ፡፡ የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው በጤናው ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ ተማሪዎችን እያፈራ ይገኛል፡፡…

መፈንቅለ መንግስቱን የመሩት ኮሎኔል አሲሚ ጎይታ የማሊ የሽግግር ጊዜ ፕሬዚዳንት ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማሊ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ወታደራዊ መሪውን ኮሎኔል አሲሚ ጎይታን የሃገሪቱ የሽግግር ጊዜ ፕሬዚዳንት አድርጎ ሰየመ፡፡ ኮሎኔል ጎይታ ከቀናት በፊት በመፈንቅለ መንግስት ስልጣኑን ከያዙ በኋላ የሃገሪቱ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት እንደሆኑ ማወጃቸው…