Fana: At a Speed of Life!

የካፍ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የካፍ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡ በዚሁ መሠረት የሴካፋ ሻምፒዮኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ÷ ከደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ፣ ከግብፁ ቱታንካሀሞን እና ከናይጄርያው ኢዲኦ ክዊንስ ጋር በምድብ ቢ ተደልድሏል።

የፕሪሚየር ሊጉ 4ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ከነገ ጀምሮ ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 4ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ከእረፍት መልስ ከነገ ጀምሮ በድሬዳዋ ስታዲየም በሚደረጉ ጨዋታዎች ይቀጥላል፡፡ በዚሁ መሠረት ነገ 10 ሠዓት ላይ ሀዲያ ሆሳዕና ከሐዋሳ ከተማ እና ምሽት 1 ሠዓት ላይ መቐለ 70 እንደርታ…

የኢትዮጵያ ሠነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ በምስራቅ አፍሪካና በኢትዮጵያ የፋይናንስ ገበያን ማጎልበት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ በምስራቅ አፍሪካና በኢትዮጵያ የፋይናንስ ገበያን ማጎልበት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ዋና ዳይሬክተር ጥላሁን ካሳሁን (ዶ/ር)፣…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ለሦስት ከፍተኛ ኃላፊነቶች ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡ በዚሁ መሠረት ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ሰላማዊት ካሳ የቱሪዝም ሚኒስትር እንዲሁም ሃና አርዓያሥላሴ የፍትሕ ሚኒስትር…

የያህያ ሲንዋር መገደል የጦርነቱ ፍጻሜ አይደለም-  ጠ/ሚ ኔታንያሁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል የሃማስ መሪ የነበሩትን ያህያ ሲንዋርን ጋዛ ውስጥ መግደሏን አረጋግጣለች፡፡ ይህን ተከትሎም የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በሰጡት መግለጫ÷ የያህያ ሲንዋር መገደል ከፍተኛ ድል ቢሆንም የጦርነቱ ፍጻሜ እንዳልሆነ…

የኢትዮጵያ እና የጀርመን ልማት ባንኮችን ትብብር ለማጠናከር ያለመ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና የጀርመን ልማት ባንክ በጋራ በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ላይ ትብብራቸውን በይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ውይይቱን ያደረጉት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት እመቤት መለሠ (ዶ/ር) እና የባንኩ ማኔጅመንት…

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጊኒ ጋር የነበረበትን የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በሽንፈት ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ከጊኒ አቻው ጋር ያደረጋቸውን ጨዋታቸው በደርሶ መልስ 7 ለ 1 መሸነፉ ይታወቃል፡፡…

በቴክኖሎጂ ፈጠራ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውድድር ኢትዮጵያውያን 3ኛ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የቴክኖሎጂ ፈጠራ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውድድር ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎች 3ኛ ደረጃ በመያዝ 4 ሺህ ዶላር ተሸለሙ፡፡ ከ48 የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ እና ታዳጊዎች የተሳተፉበት የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር የማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት በአዲስ…

የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ለሽያጭ ዝግጁ መሆን የታሪካዊ ክንውን ምዕራፍ ማሳያ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ የአክሲዮን ለሽያጭ ይፋ አድርገዋል፡፡ ይህን ተከትሎም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በዛሬው ዕለት 10 በመቶ የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ለሽያጭ ዝግጁ መሆኑ የታሪካዊ…

የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ አደረጉ፡፡ ኢትዮ-ቴሌኮም ካለው አጠቃላይ የአክሲዮን ድርሻ ውስጥ 10 በመቶውን ነው በዛሬው ዕለት ለሽያጭ ይፋ ያደረገው፡፡ የእያንዳንዱ አክሲዮን ዋጋም…