Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 7 ወራት 102 የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፈረንጆቹ ጥር ወር 2023 ጀምሮ 102 የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ማከናወኑን የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ አስታወቀ፡፡ የባንኩ ሜዲካል ዳይሬክተር እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን ትምህርት ክፍል መምህርት ዶ/ር መነን አያሌው÷ ባለፈው የፈረንጆቹ…

በደቡብ ክልል ከ573 ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ በሕገ- ወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በሕገ- ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 573 ነጥብ 5 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ መያዙ ተገለጸ። በፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠበት የአፈር ማዳበሪያ በፍጥነት ለአርሶ አደሩ እንዲሰራጭ እየተደረገ መሆኑም ተጠቁሟል።…

ከ9 ሚሊየን በላይ ብር ታክስ መንግስትን አሳጥተዋል የተባሉ ግለሰቦች በሙስና ወንጀል ተከሰሱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ9 ሚሊየን በላይ ብር ዓመታዊ የገቢ ግብር ታክስ መንግስትን አሳጥተዋል የተባሉ ሦስት ግለሰቦች በሙስና ወንጀል ተከሰሱ። ተከሳሾቹ 1ኛ በንግድ ስራ ላይ ተሰማርታለች የተባለችው ተቋራጭ አብዬ አማረ፣ 2ኛ የኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ የሒሳብ ባለሙያ ተረፈ…

የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ 6ተኛ ዙር 2ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል፡፡ በጉባዔው ላይ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ አፈ-ጉባዔ ሙህየዲን አሕመድ፣ ምክትል አፈ -ጉባዔ ዚነት ዩሱፍን ጨምሮ…

የሶማሌ ክልል ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ መስጠቱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 11 ቢሊየን 443 ሚሊየን 226 ሺህ ብር ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የሶማሌ ክልል ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ ኢብራሂም አሕመድ ለፋና…

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሀገራዊ ሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡ በውይይታቸውም÷ ሁለቱ መሪዎች በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ እና ታሪካዊ ግንኙነት በማጠናከር የንግድ…

ኢትዮጵያ ከሴራሊዮን ጋር ያላት ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከር ትፈልጋለች- አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከሴራሊዮን ጋር ያላትን የሁለትዮሽ፣ አህጉራዊ እና የባለብዙ ወገን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እንደምትፈልግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡ አቶ ደመቀ መኮንን ከሴራሊዮን ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ማዳ ቢዮ…

የአፋር ክልል የ2016 ዓ.ም በጀት ከ11 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ ፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል የ2016 ዓ.ም በጀት ከ11 ቢሊየን 993 ሚሊየን ብር በላይ ሆኖ ጸደቀ፡፡ የአፋር ክልል ምክር ቤት በመደበኛ ጉባዔው የክልሉን የ2016 ዓ.ም በጀት መርምሮ አፅድቋል። የበጀት እጥረት ችግርን በመቅረፍ ረገድ የገቢ አቅምን…

በትግራይ ክልል ከ55 ሺህ በላይ ታጣቂዎች ወደ ሕብረተሰቡ ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የነበሩ ከ55 ሺህ በላይ ታጣቂዎች ወደ ሕብረተሰቡ መቀላቀላቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ም/ርዕሰ መስተዳድርና ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ጀነራል ታደሰ ወረደ ገለጹ፡፡ ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ በፕሪቶሪያው…

የሰው ሀብት ለዘላቂ ልማት መግቢያ መንገድ ነው- አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰው ሀብት ልማት ለዘላቂ ልማት መግቢያ መንገድ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በታንዛኒያ…