Fana: At a Speed of Life!

ሲዳማ ቡና መቻልን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሲዳማ ቡና መቻልን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ቀን 7፡00 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች ያሬድ ባየህ በፍጹም ቅጣት ምት እና በጨዋታ…

ከማርበርግ ቫይረስ ታካሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው – ዶ/ር መቅደስ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከማርበርግ ቫይረስ ታካሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው 349 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው አሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ። ሚኒስትሯ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ፥ እስካሁን የማርበርግ ቫይረስ ምርመራ ከተደረገላቸው 73 ሰዎች…

ከ17 ዓመት በታች የሴካፋ ዋንጫ ኢትዮጵያ ከኬንያ የሚያደርጉት ጨዋታ በፋና+

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ማጣሪያ ውድድር ከምድባቸው ማለፋቸውን ያረጋገጡት ኢትዮጵያ እና ኬንያ ዛሬ 10፡00 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ። ጠዋታው በፋና+ ቴሌቪዥን ቻናል እና በፋና ዲጂታል አማራጮች በቀጥታ ይተላለፋል። እኩል 7…

ፕሬዚዳንት ታዬ ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከቼክ ሪፐብሊክ፣ ሃንጋሪ፣ ስሎቫክያ እና ክሮሽያ ሀገራት መሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ታዬ ከመሪዎቹ ጋር የመከሩት በ7ኛው የአፍሪካ አውሮፓ ህብረቶች ጉባዔ ጎን ለጎን ነው። ውይይቱ በዋናነት በሀገራቱ…

የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በተለያዩ አከባቢዎች ያካሄዱት የልማት ሥራ ጉብኝት…

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡ አመራሮቹ ባለፉት ቀናት በ2ኛ ዙር “የመደመር መንግሥት ዕይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሃሳብ የተሰጠውን ሥልጠና ሲወስዱ ቆይተዋል፡፡…

የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የመዲናዋ የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልጽግና አመራሮች በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡ አመራሮቹ “የመደመር መንግሥት ዕይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሃሳብ ባለፉት ቀናት ስልጠና ሲወስዱ መቆየታቸው ተመላክቷል፡፡ በዛሬው…

በቡድን 20 ጉባዔ ውጤታማ ስብሰባዎች ተካሂደዋል – ቢልለኔ ስዩም

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቡድን 20 ጉባዔ አመርቂ እና ውጤታማ ስብሰባዎች ተካሂደዋል አሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም። ቢልለኔ ስዩም በቡድን 20 የመሪዎች ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያን ተሳትፎ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ እንዳሉት፤…

ኮፕ32ን ስናዘጋጅ ከብራዚል የምንወስደው ጠቃሚ ልምዶች አሉ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኮፕ32ን በኢትዮጵያ ስናዘጋጅ ከብራዚል የምንወስደው ብዙ ጠቃሚ ልምዶች አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቡድን 20 አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን ከብራዚሉ ፕሬዚዳንት ሉዊዝ ኢናችዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከካፍ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሲፒ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከካፍ ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሲፒ (ዶ/ር)…

አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኢጋድ ዋና ጸኃፊ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን ለምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ጸኃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) አቅርበዋል። ዋና ጸኃፊው ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት፤ ከአምባሳደር…