Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ስፓርት

ግብፅ በኢትዮጵያ ከገጠማት መራር ሽንፈት በኋላ አሰልጣኟን አሰናበተች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብፅ እግር ኳስ ማህበር የብሄራዊ ቡድኑን አሰልጣኝ ኢሀብ ጋላልን ከአሰልጣኝነት አሰናበተ። ግብጽ የዛሬ ሳምንት ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ጨዋታዋን በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከጨዋታ ብልጫ ጋር 2 ለ 0 መሸነፏ ይታወሳል። ከዚህ ባለፈም…

በፕሪሚየር ሊጉ ጅማ አባ ጅፋር እና ፋሲል ከነማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ26ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጅማ አባ ጅፋር ሃድያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ረፋድ ላይ በተደረገው ጨዋታ አንጋፋው ዳዊት እስጢፋኖስ ከረጅም ጊዜ በኋላ ባስቆጠራት ጎል ጅማ አባ ጅፋር ሙሉ ሶስት ነጥብ ማግኘት ችሏል፡፡…

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 8፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በ26ኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ በባህርዳር ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አዳማ ከተማ እስከ እረፍት በአሜ መሀመድ ብቸናኛ ጎል ሲመራ ቢቆይም ከዕረፍት መልስ አቡበከር ናስር ያስቆጠራቸው…

ከዕረፍት በተመለሰው ፕሪሚየር ሊግ አርባ ምንጭ ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከዕረፍት መልስ ዛሬ ተካሂዷል። ረፋድ ላይ ሲዳማ ቡናን ከአርባ ምንጭ ከተማ ባገናኘው ጨዋታ አርባ ምንጭ አሸናፊ ሆኗል። ጨዋታው 2 ለ 1 ሲጠናቀቅ ኤሪክ ካፓይቶ ሁለቱን የማሸነፊያ ጎሎች…

በግብፅ የተመዘገበው ድል የብሄራዊ ቡድኑን ጥንካሬ የሚያሳይ ነው-አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብፅ የተመዘገበው ድል የብሄራዊ ቡድኑን ጥንካሬ የሚያሳይ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ  ቆይታውን በተመለከተ የቡድኑ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋዜጣዊ መግለጫ…

ኢትዮጵያ በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች። በውድድሩ ኢትዮጵያ በ4 ወርቅ፣ 6 ብር እና 4 ነሃስ በአጠቃላይ በ14 ሜዳልያ 5ኛ ደረጃ ይዛ ማጠናቀቋን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል። በውድድሩ…

በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያ አገኘች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች። ዛሬ በተካሄዱ ውድድሮች በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሴቶች ኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳልያ አግኝታለች። በውድድሩ አትሌት ወርቁውሃ ጌታቸው እና ዘርፌ ወንድማገኝ…

አትሌት ማሞ መንግስቱና አትሌት ዝናሽ ጋረደው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድርን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ማሞ መንግስቱና አትሌት ዝናሽ ጋረደው በባህር ዳር ከተማ የተካሄደውን 38ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር አሸነፉ፡፡ በውድድሩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ…

ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 7ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ “አዲስ አበባ የሰላምና የአብሮነት ከተማ” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ተካሄደ። በክፍለ ከተማው መድሃኔአለም አደባባይ ላይ በተካሄደው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የከተማ አስተዳድሩ ምክትል ከንቲባ…

ኢትዮ-ሰላም ሩጫ በወላይታ  በሚል መሪ  ቃል በወላይታ ሶዶ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ኢትዮ-ሰላም ሩጫ በወላይታ በሚል መሪ  ቃል በወላይታ ሶዶ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄዷል፡፡ ሩጫው የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ታላላቅ አትሌቶች በተገኙበት ተካሂዷል ። የጎዳና ላይ ሩጫው 5 ኪሎ ሜትር መንገድ የሸፈነ ሲሆን፥…