Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
በናይጄሪያ የነዳጅ ምርቶችን በሚያጓጓዝ መኪና ላይ በደረሰ አደጋ የ20 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በናይጄሪያ የነዳጅ ምርቶችን ሲያጓጉዝ በነበረ አንድ የጭነት መኪና ላይ በተከሰተ ፍንዳታ የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡
አደጋው የተከሰተው በደቡባዊ ናይጄሪያ የኢዶ እና ዴልታ ግዛቶችን በሚገናኝ አውራ ጎዳና ዋና መስቀለኛ መንገድ…
በየመን የሚስተዋለው የረሃብ አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ መሆኑን ተመድ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየመን የሚስተዋለው የረሃብ አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ መሆኑን አስታውቋል።
ድርጅቱ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት በእርስ በርስ ጦርነት እየታመሰች የምትገኘው የመን ዜጎች በግጭት፣ በድህነት፣ በጎርፍ አደጋ…
ቻይና ሂዩስተን የሚገኘውን ቆንስላዋን እንድትዘጋ አሜሪካ አዘዘች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና ቴክሳስ ሂዩስተን የሚገኘውን ቆንስላዋን እንድትዘጋ አሜሪካ ትዕዛዝ ማስተላለፏ ተገለፀ።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ውሳኔው የተላለፈው የአሜሪካ የአዕምሯዊ ንብረቶችን ለመጠበቅ ሲባል ነው ብሏል።
ቻይና የአሜሪካን…
ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን በሶሪያ የሚገኙ የቱርክ ወታደሮች ባሉበት እንደሚቆዩ አስታወቁ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን በሶሪያ የሚገኙ የቱርክ ወታደሮች ባሉበት እንደሚቆዩ አስታወቁ፡፡
ፕሬዚዳንቱ የሶሪያውያን ሰላምና መረጋጋት እስከሚመለስ ድረስ የቱርክ ወታደሮች በሶሪያ ይቆያሉ ብለዋል፡፡
ቱርክ ወታደሮቿን ከፈረንጆቹ…
ዚምባብዌ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ሰአት እላፊ አወጀች
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዚምባብዌው ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ሰአት እላፊ አወጁ፡፡
ሰአት እላፊው የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በማሰብ የታወጀ ነው ተብሏል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ከዛሬ ጀምሮ የታወጀውን ሰአት እላፊ የፀጥታ አካላት እንዲያስተገብሩም ትዕዛዝ…
የአውሮፓ ህብረት ሀገራት መሪዎች ለድህረ ኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ የ859 ቢሊየን ዶላር በጀት ላይ ከስምምነት ደረሱ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት መሪዎች ከ4 ቀናት ተከታታይ ስብሰባ በኋላ የድህረ ኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ በጀት ዙሪያ ከስምምነት መድረሳቸው ተገለፀ።
የህብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች ከስምምነት የተደረሱበት የበጀት ማዕቀፍ 859 ቢሊየን የአሜሪካ…
በግብፅ እስር ቤቶች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እየተስፋፋ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 14 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በግብፅ እስር ቤቶች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እየተስፋፋ መሆኑን ሂውማን ራይትስ ዎች አስታወቀ።
በዚህም በግብፅ የእስር ማእከላት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ቢያንስ 14 እስረኞች መሞታቸውን ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት ገልጿል ፡፡
በሀገሪቱ…
በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ፍጥነት አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል-የዓለም ጤና ድርጅት
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ፍጥነት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
የዓለም ጤና ድርጅት በትናንትናው እለት እንዳስታወቀው በተለይም በደቡብ አፍሪካ እየታየ ያለው በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት መጨመር…
በሰው ላይ የተሞከረው ክትባት የሰዎችን የኮሮና ቫይረስ የመከላከል አቅም ማሻሻሉ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው የኮሮና ቫይረስ ክትባት በሰው ላይ ተሞክሮ መልካም ውጤት ማሳየቱ ተነገረ።
በዩኒቨርሲቲው የተዘጋጀው ይህ ክትባት ደህንነቱ የተጠበቀ እና የሰዎችን የበሽታ የመከላከል አቅም እንደሚያሻሽል መረጋገጡን ቢቢሲ ዘግቧል።…
200 ዓመታትን ያስቆጠረው በህንድ የሚገኝ መስጊድ በከባድ ዝናብ ጉዳት ደረሰበት
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህንድ ዋና ከተማ ኒው ዴሊህ የሚገኘው 200 ዓመታትን ያስቆጠረው መስጊድ በከባድ ዝናብ ምክንያት ጉዳት እንደደረሰበት ተነገረ።
ከቀይ የሸክላ ድንጋይ በፈረንጆቹ 1823 ዓ.ም እንደተገነባ የሚነገረው መስጊዱ በከተማዋ ከሚገኙ ጥቂት ጥንታዊና ታሪካዊ…