Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

በቻይና የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች  ቁጥር ለተካታታይ ሶስት ቀናት ቅናሽ አሳየ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ለተከታታይ ሶስት ቀናት ቅናሽ ማሳየቱን አስታወቀች። የሀገሪቱ ባለስልጣናት በዛሬው ዕለት እንዳስታወቁት በሀገር አቀፍ ደረጃ 2 ሺህ 9 አዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች ሲመዘገቡ 142 ሰዎች ህወይታቸው አልፏል።…

የደቡብ ሱዳን መንግስት የሀገሪቱ ግዛቶች ቁጥር ከ32 ወደ 10 ዝቅ እንዲል ወሰነ

አዲስ አበባ፣የካቲት 7፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የሀገሪቱ ግዛቶች ቁጥር ከ32 ወደ 10  ዝቅ እንዲል መስማማታቸውን ይፋ አድርገዋል። ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጉዳዩን አስመልክተው በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ፥ በሀገሪቱ የተጀመረው የሽግግር መንግስት ምስረታ ሂደት…

በአውሮፓ በኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያው ሰው ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ በኮሮና ቫይረስ በሽታ ከተያዙ ሰዎች መካከል የመጀመሪያው ሰው ህይወት ማለፉ ተሰምቷል። በፈረንሳይ ህይወታቸው ያለፉት የ80 ዓመቷ አዛውንት ለጉብኝት ከቻና ሁቤይ ግዛት የመጡ  መሆናቸውን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ይህም…

በማሊ በተፈጠረ ግጭት ወታደሮችን ጨምሮ 30 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በማሊ በተፈጠሩ የተለያዩ ግጭቶች 30 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ። ግጭቱ በማሊ የኦጎሳጎ መንደርን ጨምሮ በሶስት የተለያዩ ስፍራዎች የተቀሰቀሰ ነው። ከሞቱት 30 ሰዎች ውስጥ ዘጠኝ ወታደሮች በወታደራዊ ጣቢያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት…

ሱዳን በፈረንጆቹ 2000 በአሜሪካ መርከብ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ለተጎጂ ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ተስማማች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሱዳን በፈረንጆቹ 2000 በአሜሪካ መርከብ ላይ በደረሰው ፍንዳታ ተጎጂ ለሆኑ 17 ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ተስማማች። በወቅቱ ዩ ኤስ ኤስ ኮል በተባለችው መርከብ ላይ አልቃይዳ በየመን ወደብ በፈጸመው ጥቃት 17 የአሜሪካ ባህር ሃይል አባላት…

ሩሲያ በሶሪያ ኢድሊብ ግዛት ጥቃት አለመፈጸሟን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በሶሪያ ኢድሊብ ግዛት በንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃት ፈጽማለች በሚል የቀረበባትን ውንጀላ አስተባበለች። በቅርቡ ሩሲያ በኢድሊብ ግዛት ፈጽማዋለች በተባለው ጥቃት በጥቂቱ የ14 ንጹሃን ዜጎች ህይወት ማለፉን መቀመጫውን ብሪታኒያ ያደረገው የሶሪያ…

በናይጄሪያ በላሳ ትኩሳት የሟቾች ቁጥር ወደ 70 ከፍ ብሏል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በናይጄሪያ በላሳ ትኩሳት ወረርሽኝ የሟቾች ቁጥር ወደ 70 ከፍ ማለቱ ተነገረ። በወረርሽኙ ተይዘዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰወች ቁጥር ደግሞ ከ700 ወደ 1 ሺህ 708 ከፍ ማለቱ ተነግሯል። የናይጄሪያ የበሽታ መቆጣጠር ማዕከል ባለፈው ሳምንት…

በቻይና ሁቤይ ግዛት በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ማሻቀቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ሁቤይ ግዛት በኮሮና ቫይረስ አዲስ የሚያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተነገረ። በግዛቲቱ ትናንት ብቻ ወደ 242 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰምቷል። ከዚህ ባለፈም 14 ሺህ 840 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፥…

የሩሲያ የቀድሞው የማረሚያ ቤት ሀላፊ ፍርድ ቤት ውስጥ ራሱን አጠፋ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሩሲያ የቀድሞው የማረሚያ ቤት አገልግሎት ሃላፊ ፍርድ ቤት ውስጥ ራሱን ማጥፋቱ ተነግሯል። ቪክቶር ስቪሪዶቭ የተባለው ግለሰብ የሩሲያ ማረሚያ ቤት አገልግሎት የሞተር ትራንስፖርት ክፍል ሃላፊ ሆኖ በሚያገለግልበት ወቅት 125 ሺህ ዶላር ከምክትል…

በቻይና በኮሮና ቫይረስ አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በ48 ነጥብ 2 በመቶ ቀንሷል – የሃገሪቱ ጤና ኮሚሽን

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና በየዕለቱ በኮሮና ቫይረስ አዲስ የሚያዙ ሰወች ቁጥር በ48 ነጥብ 2 በመቶ መቀነሱን የሃገሪቱ ጤና ኮሚሽን አስታወቀ። ከፈረንጆቹ የካቲት 4 እስከ 11 ባሉት ቀናት በሃገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰወች ቁጥር መቀነሱን ነው ኮሚሽኑ…