Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
እስራኤል በሶሪያ ደማስቆ አቅራቢያ በኢራን የሚደገፉ ሀይሎች ላይ የአየር ጥቃት ፈፀመች
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) እስራኤል በሶሪያ ደማስቆ አካባቢ በሚንቀሳቀሰው እና በኢራን በሚደገፈው ሀይል ላይ እርምጃ መውሰዷ ተገለፀ።
ሳና የዜና አገልግሎት እንዳስነበበው ከእስራኤል የተተኮሱ በርካታ ሚሳኤሎችን መመከት ቢቻልም፤ ስምንት ሰዎች ላይ ግን ጉዳት ደርሷል ብሏል።…
ለጋሾች በየመን በሃውቲ ቁጥጥር ስር በሚገኙ ይዞታዎች የሚያደርጉትን ሰብአዊ እርዳታ እንደሚቀንሱ ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለጋሾች በየመን በሃውቲ አማጽያን ቁጥጥር ስር በሚገኙ ይዞታዎች የሚያደርጉትን ሰብዓዊ ድጋፍ ሊቀንሱ እንደሚችሉ አስታወቁ።
ለዚህም በአካባቢው ያለው ሁኔታ ለስራቸው እንቅፋት መሆኑን ገልጸዋል።
በአካባቢው ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ሳቢያም ሰብዓዊ ድጋፉ…
በቻይና አዲስ የተወለደ ጨቅላ ህጻን በኮሮና ቫይረስ ተያዘ
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና ውሃን ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል የተወለደ ጨቅላ ህጻን በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተሰማ።
ህጻኑ ከተወለደ ከ30 ሰዓታት በኋላ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መሆኑን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ይህም በቫይረሱ የተያዘ በእድሜ ትንሹ ሰው…
በቱርክ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 170 ሰዎች ተጎድተዋል
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቱርክ ኢስታንቡል በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል።
አውሮፕላኑ በኢስታንቡል አውሮፕላን ማረፊያ በማረፍ ላይ እያለ ከማኮብኮቢያው ተንሸራቶ በመውጣቱ አደጋው ደርሷል።
በዚህ ሳቢያም አውሮፕላኑ ሶስት ቦታዎች ላይ…
በቻይና በኮሮና ቫይረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 563 ደረሰ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ500 በላይ መድረሱ ተነገረ።
እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ የሟቾቹ ቁጥር 563 መድረሱን መረጃዎች ያመላክታሉ።
በትናንትናው እለት ብቻ በሁቤይ ግዛት 70 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል።…
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከቀረቡባቸው ክሶች ነፃ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከስልጣን እንዲነሱ ከቀረቡባቸው ክሶች ነጻ ሆነዋል።
ፕሬዚዳንቱ ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀምና የምክር ቤቱን ስራ በማደናቀፍ ክስ ቀርቦባቸው የክርክር ሂደቱ ሲታይ ቆይቷል።
ትራምፕ በበኩላቸው…
ፊንላንድ ለወንዶች ከሴቶች እኩል የወሊድ ፈቃድ ልትሰጥ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፊላንድ ለወንዶች ከሴቶች እኩል የወሊድ ፈቃድ ልትሰጥ መሆኑ ተነገረ።
አሁን ባለው አሰራር በፊንላንድ የወለዱ እናቶች ከአራት ወራት በላይ የወሊድ ፈቃድ ሲያገኙ ወንዶች ደግሞ ሁለት ወር ከሁለት ሳምንት ፈቃድ ማግኘት ይችላሉ።
ውሳኔው አባቶች…
የሌሶቶ ቀዳማዊት እመቤት የባለቤታቸውን የቀድሞ ሚስት በመግደል ክስ ተመሰረተባቸው
አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሌሶቶ ቀዳማዊት እመቤት ማይሲያህ ታባኔ የባለቤታቸውን የቀድሞ ሚስት በመግደል ክስ ተመሰረተባቸው።
ሊፖሌሎ ታባኔ የቀድሞ ባለቤታቸው ቶማስ ታባኔ በፈረንጆቹ ሰኔ ወር 2017 ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ቃለ መሃላ ከመፈፃማቸው ሁለት ቀናት አስቀድሞ…
ኢራን ለሲ አይ ኤ ሲሰልል ነበር ባለችው ግለሰብ ላይ የሞት ቅጣት አስተላለፈች
አዲስ አበባ፣ጥር 27፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን ለአሜሪካው የስለላ ድርጅት (ሲ አይ ኤ) መረጃ አሳልፎ ሲሰጥ ነበር ባለችው ግለሰብ ላይ የሞት ቅጣት አስተላለፈች።
የኢራን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሚር ራሂምፖው የተባለው ተከሳሽ የሀገሪቱን የኒውክሌር ፕሮግራም የሚመለከቱ የተለያዩ መረጃዎችን…
የፕሬዚዳንት ትራምፕ ንግግር ቅጂ በኮንግረሱ አፈ ጉባኤ መቀደድ እያነጋገረ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ታላቋን አሜሪካ እንመልሳለን ሲሉ ትናንት በዓመቱ የኮንግረሱ የመክፈቻ ንግግራቸው ላይ አንስተዋል።
የትራምፕ ንግግር በአሜሪካ ኮንግረስ በመገኘት የመንግስታቸውን እና የህግ አውጭውን አካል እቅድ የሚጠቁሙበት…