Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
የዓለም ጤና ድርጅት ኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት መሆኑን አወጀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት መነሻውን ቻይና ያደረገውን የኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ነው በሚል አወጀ።
ድርጅቱ ቫይረሱን በዓለም አቀፍ የጤና ስጋትነት ያወጀው ከቻይና ውጭ ወደ ሌሎች ሀገራት መዛመቱን ተከትሎ ነው ተብሏል።
የዓለም ጤና…
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በዛሬው ዕለት በሩሲያ ሞስኮ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሞስኮ ቆይታቸውም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም የሀገራቱን የሁለትዮሽ…
በአሜሪካ እና ሜክሲኮ ድንበር አቅራቢያ ረጅሙ ዕፅ ማዘዋወሪያ ዋሻ ተገኘ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ እና ሜክሲኮ ድንበር አቅራቢያ ረጅሙን የዕፅ ማዘዋወሪያ ዋሻ ማግኘታቸውን የአሜሪካ ባለስልጣናት አስታወቁ።
ዋሻው አሜሪካን ከሜክሲኮ ጋር በሚያዋስናት ድንበር በኩል ዕፅ አዘዋዋሪዎች ይጠቀሙበት እንደነበረም ገልጸዋል።
1 ሺህ 313…
በቻይና የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከ7 ሺህ በላይ ደረሰ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 7 ሺህ 711 መድረሱን የሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በቫይረሱ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 170 መድረሱንም ነው የገለጸው።
የቫይረሱ ስርጭትም በመላው ቻይና መስፋፋቱን ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች…
የሶሪያ ወታደሮች በአማጽያን ቁጥጥር ስር የነበረች ቁልፍ ከተማን አስለቀቁ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2012 (ኤፍ ቢሲ) የሶሪያ መንግስት ወታደሮች በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር የነበረች ወሳኝ ከተማን ነጻ ማውጣታቸው ተሰምቷል።
የሶሪያ ጦር በሀገሪቱ ሰሜን ምዕራብ ክፍል ኢድሊብ ግዛት ባካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር የነበረችውን ማራት አል ኑማ ከተማን…
ዶናልድ ትራምፕ አዲሱን የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም እቅድ ይፋ አደረጉ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አዲሱን የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም እቅድ ይፋ አደረጉ።
ትራምፕ የሰላም እቅዱን ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ይፋ አድርገውታል።
በአዲሱ የሰላም እቅድ የፍልስጤማውያን ሉዓላዊ ግዛት…
በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ ከቻይና በመጡ የቤተሰብ አባላት ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኘ
አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ ከቻይና በመጡ የቤተሰብ አባላት ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በቫይረሱ ተይዘዋል የተባሉት የቤተሰብ አባላት የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ…
አሜሪካና ኢራቅ ባግዳድ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዙ
አዲስ አበባ፣ጥር 19፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ እና ኢራቅ ሰሞኑን ባግዳድ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ የተፈጸመውን የሮኬት ጥቃት አውግዘዋል።
የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር አዴል አብዱል መሃዲ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም…
ዶ/ር ቴድሮስ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በቤጂንግ ተገናኝተው ተወያዩ።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ለመምከር…
ኢራን በባለስቲክ ሚሳኤሎች ፋንታ ሳተላይት ለማምጠቅ መዘጋጀቷን አስታወቀች
አዲስ አበባ፣ጥር 19፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢራን በባለስቲክ ሚሳኤሎች ፋንታ ሳተላይት ለማምጠቅ ቦታ ማዘጋጀቷን አስታውቃለች፡፡
የሃገሪቱ የመረጃና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር መሀመድ ጃቫድ ዛሪ ዛፋር ሳተላይትን ወደ ምህዋር ለመላክ አንድ ጣቢያ እየተዘጋጀ ነው ሲሉ በትዊተር ገጻቸው…