Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

ከሚሳኤል ጥቃቱ በኋላ የኢራን ውድቀት  እየታየ ነው- ዶናልድ ትራምፕ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ  ኢራን በአሜሪካ የጦር መንደር ላይ ጥቃት ከፈፀመች በኋላ  ውድቀቷ እየታየ ነው ሲሉ ገለፁ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ኢራን  በኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር መንደር ላይ የፈፀመችውን ጥቃት በተመለከተ መግለጫ…

ኢራን በአሜሪካ የጦር መንደር ላይ ጥቃት ከፈፀመች በኋላ የነዳጅ ዋጋ ማሻቀቡ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን ኢራቅ በሚገኙ ሁለት የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት መፈፀሟን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ከፍ ማለቱ ተሰምቷል፡፡ በዚህም ያልተጣራ አንድ በርሚል የነዳጅ ዘይት በ1 ነጥብ 4 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በመካከለኛው እስያ በ69 ነጥብ 21 ዶላር…

በሶማሊያ ፓርላማ አቅራቢያ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት አራት ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ፓርላማ አቅራቢያ በተፈጸመ ቦምብ ጥቃት በርካቶች ለህልፈት መዳረጋቸው ተነገረ። በፍተሻ ጣቢያ አካባቢ በተፈጸመው ጥቃት እስካሁን አራት ሰዎች ሲሞቱ ከ10 ሰዎች በላይ መቁሰላቸው ተነግሯል። ለጥቃቱ አልሸባብ ኃላፊነቱን…

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኩፍኝ ወረርሽኝ ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኩፍኝ ወረርሽኝ እስካሁን ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። የዓለም ጤና ድርጅት የበሽታው ስርጭት እጅግ ፈጣን መሆኑንም አስታውቋል። ካለፈው የፈረንጆቹ አመት መጀመሪያ…

170 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ቦይንግ 737 አውሮፕላን ኢራን ውስጥ ተከሰከሰ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29 ፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ንብረትነቱ የዩክሬን አየር መንገድ የሆነው ቦይንግ 737 አውሮፕላን 170 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ ኢራን ውስጥ ተከስክሷል። አውሮፕላኑ ከኢራን ዋና ከተማ ቴህራን አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ወደ ዩክሬቭ መዲና ኬቭ መብረር ከጀመረ ከጥቂት ደቂቃዎች…

ኢራን በኢራቅ በሚገኝ የአሜሪካ የዓየር ሀይል ሰፈር ላይ የሚሳኤል ጥቃት ፈፀመች

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢራን በኢራቅ በሚገኝ የአሜሪካ ዓየር ሀይል የጦር ሰፈር ላይ የባለስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ፈፀመች። የአሜሪካ የመከላከያ መስሪያ ቤት ፔንታጎን ሁለት የጦር ሰፈሮች ጥቃት እንደተፈፀመባቸው አስታውቋል። የኢራን የመንግስት ቴሌቪዥን ጣቢያ…

በኢራን የጄነራል ቃሲም ሱለይማኒን ቀብር ላይ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ የ35 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢራን የጄነራል ቃሲም ሱለይማኒን ቀብር ላይ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ በትንሹ የ35 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል። የኢራን ብሄራዊ አብዮት ዘብ ጠባቂ ሃይል አዛዥ ጄነራል ቃሲም ሱለይማኒን ባሳለፍነው ሳምንት በኢራቅ ውስጥ በአሜሪካ…

ቻይና አሜሪካ እና ኢራን በመካከላቸው የተፈጠረውን ውጥረት በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 28፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና የተፈጠረው አለመግባባት በውይይት ሊፈታ እንደሚገባ አሳሰበች። አሜሪካ ባሳለፍነው ሳምንት በመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ የነበሩትን የኢራን ብሄራዊ አብዮት ዘብ ጠባቂ ሃይል አዛዥ ጀኔራል ቃሲም…

ቱርክ ወታደሮቿን ወደ ሊቢያ መላክ ጀመረች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቱርክ ፕሬዚዳናት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን የሀገሪቱ ወታደሮች ፓርላማው ያሳላፈውን ውሳኔ ተከትሎ ወደ ሊቢያ ማቅናት መጀመራቸውን አስታወቁ። ወደ ሊቢያ ማቅናት የጀመሩት ወታደሮች ተልዕኮ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈውን የትሪፖሊ መንግስት…

ሺንዞ አቤ በመካከለኛው ምስራቅ ሃይል የማስፈር እቅድ እንዳላቸው በድጋሚ ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በመካከለኛው ምስራቅ ሃይል የማስፈር እቅድ እንዳላቸው በድጋሚ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የጃፓን መርከቦችን ደህንነት ለማረጋገጥ በስፍራው ሃይል የማስፈር እቅድ እንዳላቸው ገልጸዋል።…