Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

በፓኪስታን ኩዌታ በአይ ኤስ በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት የሟቾች ቁጥር 15 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፓኪስታን ደቡብ ምእራብ ኩዌታ ከተማ በመስጊድ ላይ በተፈፀመ የቦብም ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 15 መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ። በአርብ ፀሎት ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ በተፈፀመው የቦምብ ጥቃቱ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪም ከ20 በላይ ሰዎች ላይ የተለያየ…

ኢራን የዩክሬንን የመንገደኞች አውሮፕላን መታ መጣሏን አመነች

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢራን የዩክሬንን የመንገደኞች አውሮፕላን “በተፈጠረ ስህተት” መታ መጣሏን አመነች። ቴህራን አውሮፕላኑ ታስቦበት ሳይሆን በተፈጠረ ስህተት መመታቱን አስታውቃለች። አውሮፕላኑ የኢራን ብሄራዊ አብዮታዊ ዘብ ጠባቂ በሚገለገልበት “የተከለከለና ጥብቅ…

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ በኤርትራ ጉብኝት እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ሞሃመድ ፋርማጆ በኤርትራ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው። ፕሬዚዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው እለት አስመራ ሲገቡ፥ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል…

የአሜሪካ ምክር ቤት የትራምፕን በኢራን ላይ ጦር የማዝመት ስልጣን ገደበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን በኢራን ላይ ጦር የማዝመት ስልጣን የሚገድብ ውሳኔ አሳለፈ። ውሳኔው ዴሞክራቶች በተቆጣጠሩት ምክር ቤት 224 ለ194 በሆነ ድምጽ አልፏል። ይህም ትራምፕ ሃገራቸው ከቴህራን ጋር…

ሩሲያ እና ቱርክ በሶሪያ ኢድሊብ የተኩስ አቁም ስምምነት ደረሱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሩሲያ እና ቱርክ በሶሪያ ኢድሊብ ግዛት የተኩስ አቁም ስምምነት መድረሳቸውን አስታወቁ። ስምምነቱ የሶሪያ መንግሥት በተቃዋሚዎች ላይ የሚፈጽመውን ጥቃት ለማስቆም እና በአካባቢው ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ያለመ ነው ተብሏል።…

የዩክሬን የመንገደኞች አውሮፕላን ከኢራን በተተኮሰ ሚሳኤል ሳይመታ እንዳልቀረ ተነገረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቴህራን የተከሰከሰው የዩክሬን የመንገደኞች አውሮፕላን ከኢራን በተተኮሰ ሚሳኤል በስህተት ሳይመታ እንዳልቀረ ተነገረ። የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ አውሮፕላኑ “በተፈጠረ ስህተት በኢራን ሚሳኤል ተመቷል” የሚል እምነት እንዳላቸው…

በኒጀር ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 25 ወታደሮች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኒጀር ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 25 ወታደሮች መገደላቸው ተሰማ። ጥቃቱ በማሊ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ ወታደራዊ ጣቢያ ላይ የተፈጸመ ሲሆን፥ ከሞቱት በተጨማሪ ስድስት ሰዎች መቁሰላቸውም ተነግሯል። ለጥቃቱ ሃላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም፥…

ኬንያ በላሙ ወደብ ሰዓት እላፊ አወጀች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኬንያ አልሸባብ በላሙ ወደብ ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ሰዓት እላፊ ማወጇ ተሰምቷል። አልሸባብ በቅርቡ ላሙ በሚገኘው የኬንያና አሜሪካ ጥምር ጦር ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት መፈጸሙ ይታወሳል። የሽብር ቡድኑ በፈጸመው ጥቃት ሶስት የአሜሪካ…

አሜሪካ ከኢራን ጋር ድርድር ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ከቴህራን ጋር ድርድር ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች። ዋሽንግተን ለፀጥታው ምክር ቤት ባስገባችው ደብዳቤ ከቴህራን ጋር ያለ ቅድመ ሁኔታ ድርድር ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች። በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር ኬሊ ክራፍት…

ሩሲያ እና ቱርክ በሊቢያ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን እና የቱርኩ አቻቸው ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን በሊቢያ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡ። ሁለቱ መሪዎች በሊቢያ ያለውን ግጭት በዘላቂነት መፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል። በዚህም…