Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

በአውስትራሊያ  ሰደድ እሳት ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ ተነገራቸው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአውስትራሊያ በተነሳው እሳት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የቪክቶሪያ ከተባለ  ግዛት ለቀው እንዲወጡ  መነገሩ ተሰማ። በአውስትራሊያ ቪክቶሪያ ግዛት ውስጥ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በጫካ የተነሳው ሰደድ እሳት እየተባባሰ በመምጣቱ አካባቢውን…

ሩሲያ ከድምፅ 27 እጥፍ የሚፈጥነውን ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል ወደ ስራ አስገባች

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ  ከድምፅ 27 እጥፍ  የሚፈጥነውን አቫንጋር ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል ወደ ስራ ማስገባቷን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር አስታወቀ፡፡ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ሚሳኤሉ ከድምፅ 27 አጥፍ በሚበልጥ ፍጥነት እንደሚጓዝ በመግለፅ ይህም…

ፊሊፒንስ ሁለት የአሜሪካ ሴናተሮችን  ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፊሊፒንስ  ሁለት የአሜሪካ ሲናተሮችን ወደ ሀገሯ ለጉብኝት እንዳይገቡ ማገድዋ ተገለፀ፡፡ የፊሊፒንስ ፕሬዚዳንት ቃል አቀባይ   በቀጣይ ወደ ፊሊፒንስ በሚገቡ የአሜሪካ ዜጎች ጠንከር ያለ የመግቢያ እቀባ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡…

በሞቃዲሾ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት በትንሹ 76 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት በትንሹ 76 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ። ጥቃቱ የትራፊክ እንቅስቃሴ በሚበዛበት የፍተሻ ጣቢያ አካባቢ በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ ቦምብ የተፈጸመ ነው። ፖሊስ በበኩሉ ጥቃቱ በከተማዋ የሚገኝን…

ሩሲያ፣ ቻይና እና ኢራን የጋራ የባህር ሃይል ልምምድ ጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ፣ ቻይና እና ኢራን የጋራ የባህር ሃይል ልምምድ ጀመሩ። ለአራት ቀናት ይቆያል የተባለው ልምምድ በህንድ ውቅያኖስ እና የኦማን የባህር ሰርጥ ላይ ነው እየተካሄደ ያለው። የሩሲያ የባህር ሃይል ልምምዱን የተቀላቀለ ሲሆን፥ ቻይና…

በፊሊፒንስ በደረሰው የአውሎ ንፋስ አደጋ የሟቾች ቁጥር 28 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፊሊፒንስ በደረሰው አውሎ ነፋስ አደጋ የሟቾች ቁጥር 28 መድረሱ ተሰማ። የፊሊፒንስ ብሄራዊ የአደጋ ስጋት ቅነሳ እና አመራር ምክር ቤት ማዕከላዊ የሃገሪቱን ክፍል ጨምሮ በ10 የተለያዩ ቦታዎች ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል። በአደጋው ከሞቱት…

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ፓርቲያቸውን ለመምራት የተደረገውን ምርጫ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 17፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የሊኩድ ፓርቲን ለመምራት የተደረገውን ምርጫ አሸነፉ። ከሊኩድ ፓርቲ  116  ሺህ አባላት መካከል 49 በመቶ ያህሉ ድምጽ የሰጡ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥም ኔታኒያሁ  የ72 ነጥብ 5 በመቶዎቹን ድምፅ በማግኘት…

ኤርዶኻን ቱርክ በተቻለ ፍጥነት ወታደሮችን ወደ ሊቢያ እንደምትልክ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ቱርክ በተቻለ ፍጥነት ወታደሮችን ወደ ሊቢያ እንደምትልክ አስታወቁ። ሊቢያ ወታደራዊ ድጋፍ መጠየቋን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ ሃገራቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና ለሰጠው ለፋይዝ አል ሳራጅ መንግስት…

በካዛኪስታን በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የ14 ሰዎች ህይዎት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 17 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በካዛኪስታን በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ በጥቂቱ 14 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ። ንብረትነቱ ቤክ ኤር የተሰኘው አየር መንገድ የሆነው አውሮፕላን ከተነሳ ከደቂቃዎች በኋላ መከስከሱ ነው የተነገረው። በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪ 60 ሰዎች…

ጃፓን ከ2007 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ሃገር ዜጋን በሞት ቀጣች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጃፓን ከፈረንጆቹ 2007 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ሃገር ዜጋን በሞት መቅጣቷ ተነገረ። የ40 ዓመቱ ቻይናዊ ዌይ ዌይ አራት የቤተሰብ አባላትን ህይወት ማጥፋቱን ተከትሎ ቶኪዮ በሞት መቅጣቷ ነው የተነገረው። ቅጣቱ በሞት የተቀጡ ጥፋተኞች…