Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

በኢራቅ የሚገኘው የአሜሪካ  ኤምባሲ በተቃዋሚዎች ጥቃት ደረሰበት

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2012(ኤፍቢሲ) አሜሪካ በኢራን የሚደገፈው የኢራቅ ታጣቂ ሀይል የአየር ጥቃት በመፈፀሟ የተቆጡ ኢራቃውያን በባግዳድ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ፈፅመዋል፡፡ ተቃዋሚዎቹ የኤምባሲውን  የውጨኛ ክፍል ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ የአሜሪካ ወታዳሮች ወደ…

አልሸባብ  የ81 ሰዎች ህይወት ላለፈበት የሞቃዲሾ የቦንብ ጥቃት ሃላፊነቱን ወሰደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2012(ኤፍቢሲ) የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ለደረሰ  የቦንብ ፍንዳታ ኃላፊነቱ መውሰዱን አስታወቀ፡፡ ሆኖም የሶማሊያ ብሄራዊ የደህንነት ኤጀንሲ ጥቃቱ በሌላ ሀገር ታቅዶ የተፈፀመ መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡ ጥቃቱ በከተማዋ ደቡብ ምዕራብ …

በአውስትራሊያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች  ከሰደድ እሳት ለማምለጥ ወደ ባህር ዳርቻዎች ተሰደዋል

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 21፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውስትራሊያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከሰደድ እሳት ለማምለጥ ወደ ባህር ዳርቻዎች እየተሰደዱ ነው፡፡ በአካባቢው ባለው  ከፍተኛ ሙቀት እና ንፋስ በአውስትራሊያ የተከሰተው ሰደድ እሳት ወደ ተለያዩ ግዛቶች እየተስፋፋ መሆኑ ነው የተገፀው፡፡ እሳቱ…

አሜሪካ 25 የሂዝቦላህ አባላትን መግደሏን ተከትሎ ኢራቅ እርምጃውን አውግዛለች

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 21፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢራቅ አሜሪካ በኢራን ድጋፍ በሚደረግለት የካታይብ ሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን ላይ የፈጸመችውን ጥቃት  አውግዛለች። የአሜሪካ  ባሳለፍነው እሁድ ዕለት በኢራን በሚደገፉ ታጣቂዎች ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት 25 የቡድኑ አባላት ህይወት ማለፉ ይታወሳል።…

ሱዳን በ27 የደህንነት መስሪያ ቤት ሰራተኞች ላይ የሞት ቅጣት አስተላለፈች

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ፍርድ ቤት መምህርን አሰቃይቶ በመግደል የተከሰሱ 27 የደህንነት መስሪያ ቤት ሰራተኞች ላይ የሞት ቅጣት አስተላልፏል፡፡ የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በህዝባዊ ተቃውሞው ወቅት በቁጥጥር ስር የዋለን መምህር…

ባለፉት 10 አመታት ጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች በሚገኙ ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች በሶስት እጥፍ መጨመራቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፈረንጆቹ 2010 ጀምሮ ጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች በሶስት እጥፍ መጨመራቸውን አስታወቀ። ድርጅቱ ካለፉት አስር አመታት ወዲህ በህጻናት ላይ ከ170 ሺህ በላይ ከባድ የህግ…

በቻይና አንድ ህንፃ ላይ በደረሰ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ምዕራብ ቻይና በአንድ ህንፃ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ስድስት ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ፡፡ ቃጠሎው የደረሰ በደቡብ ምዕራብ ቻይና ቾንግኪንግ ማዘጋጃ ቤት ፍሊንግ አውራጃ ውስጥ ነው። አደጋው አንድ የመኖሪያ ህንፃ ባደረሰው…

ኪም ጆንግ ኡን ሰሜን ኮሪያ “ማጥቃትን መሰረት ያደረገ የደህንነት ፖሊሲ” እንደሚያስፈልጋት ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆን ኡን ሃገራቸው “ማጥቃትን መሰረት ያደረገ የደህንነት ፖሊሲ” እንደሚያስፈልጋት ተናገሩ። ኪም በፓርቲያቸው ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ፒዮንግያንግ “አዎንታዊ እና ማጥቃትን መሰረት ያደረገ የደህንነት ፖሊሲ…

በባንግላዴሽ በከፍተኛ ቀዝቃዜ የ50 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በባንግላዴሽ በተከሰተ ከፍተኛ ቀዝቃዜ የ50 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ። እሁድ በሀገሪቱ ሰሜን ጠረፍ በምትገኘው ቱቶልያ ከተማ ውስጥ 4 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ የተመዘገበ ዝቅተኛው የሙቀት መጠን   መሆኑን ተገልጿል። በመላው ሀገሪቱ…

በአሜሪካ ቴክሳስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በተከፈተ ተኩስ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ ቴክሳስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በተከፈተ ተኩስ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ። ጥቃት አድራሹ ሁለት ምዕመናንን ከገደለ በኋላ በተከፈተ የአጸፋ ተኩስ መገደሉን ፖሊስ አስታውቋል። በወቅቱ ግለሰቡ ጥቃቱን የፈጸመበትን ምክንያት እያጣራ…