Fana: At a Speed of Life!
Browsing Tag

የተመረጡ

6ኛው የብዙሃን ስፖርት በመስቀል አደባባይ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ስድስተኛው ዙር የብዙሃን ስፖርት መርሃ-ግብር ዛሬ በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል። አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግን ባህል ያደረገ ከተማ እና ህብረተሰብ መፍጠርን ዓላማ ባደረገው በዚህ ሁነት በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።…

የኤሌክትሮኒክስ አንድ መስኮት አገልግሎት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤሌክትሮኒክስ አንድ መስኮት አገልግሎት በዛሬው እለት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ይፋ ሆነ። በአገልግሎቱ ይፋ ማድረጊያ ስነ ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች የተለያዩ ተቋማት መሪዎች እና…

ብልፅግና ፓርቲ ምርጫው በዚህ አመት እንዲካሄድ ጠንካራ አቋም አለው – አቶ ብናልፍ አንዷለም

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብልፅግና ፓርቲ የ2012 ብሄራዊ ምርጫ በያዝነው አመት እንዲካሄድ ጠንካራ አቋም መያዙን አስታውቋል። የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትናንት በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ እና በሀገራዊ ምርጫው ዙሪያ ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉንም ነው…

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ትናንት ሲያካሂድ የነበረውን የመጀመሪያ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቋል። ፓርቲው ከግንባር ወደ ውህድ ፓርቲ ከተሸጋገረ በኋላ ባካሄደው የመጀመሪያ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባም በተለያዩ…

ጎተራ አካባቢ የሚገነባው የአሚባራ መንደር ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በመሃል አዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ የሚገነባው የአሚባራ መንደር ግንባታ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል። በግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂር ታከለ ኡማን ጨምሮ፣ የኢፌዴሪ የኮንስትራክሽንና የከተማ ልማት…

ህወሓት አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤውን በመቐለ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል። በጉባኤው ከህወሓት መሰረታዊ ድርጅቶች የተወከሉ አባላት፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ጥሪ የተደረገላቸው…

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከታንጀብል ሆፕ ፋውንዴሽ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከታንጀብል ሆፕ ፋውንዴሽን ድርጅት መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ሊሊ ዮሴፍ ጋር ተወያዩ። ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የፋውንዴሽኑ ተግባር ለቆሙለት አላማ ቁርጠኛ ከመሆኑም በላይ ጥሩ ውጤት እንደሚያስገኝ ገልጸዋል።…