Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ትናንት ሲያካሂድ የነበረውን የመጀመሪያ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቋል።

ፓርቲው ከግንባር ወደ ውህድ ፓርቲ ከተሸጋገረ በኋላ ባካሄደው የመጀመሪያ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባም በተለያዩ ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከሩ ተገልጿል።

በዚህ መሰረትም በስብሰባው በተነሱ የመወያያ አጀንዳዎች ላይ መግባባት ላይ በመድረስ እና የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል።

የተላለፉ ውሳኔዎችን እና የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በተመለከተም ፓርቲው በዛሬው ዕለት መግለጫ የሚሰጥ መሆኑን አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.