Fana: At a Speed of Life!

የዘንድሮው የአዲስ አበባ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የአዲስ አበባ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት “በጎነት ለዘላቂ አብሮነት” በሚል መሪ ሐሳብ በይፋ ተጀምሯል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በመጪው የክረምት ወራት በሚከናወነው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር 570 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ…

በህገ- ወጥ መንገድ 7 ሕፃናቶችን ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በህገ- ወጥ መንገድ ሰባት ሕፃናቶችን ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። ፖሊስ እንዳስታወቀው፥ ተጠርጣሪው ግለሰብ ከካፋ ዞን ጨና ወረዳ ባላ ሻሻ ቀበሌ ከአስር ዓመት በታች የሆኑ ሰባት…

በደቡብ ክልል በበልግ እርሻ 400 ሺህ ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል እየተካሄደ ባለው የበልግ እርሻ እንቅስቃሴ እስካሁን በተደረገው እንቅስቃሴ 400 ሺህ ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠው እንደገለጹት፥ በዘር የተሸፈነው መሬት…

“የተረገሙ ጦሮች” በሚል ርዕስ ከ29 አመታት በፊት የተሰራ ፊልም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለእይታ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) “የተረገሙ ጦሮች” በሚል ርዕስ ከ29 አመታት በፊት የተሰራ እና በእርቅ እና ሰላም ላይ የሚያጠነጥን ፊልም ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለእይታ ቀርቧል፡፡ ፊልሙ በደቡብ ክልል የኤርቦሬ ማህበረሰብ ዙሪያ የተሰራ ሲሆን፥ ፊልሙ በዶክተር አሉላ…

በዳኝነት ስርዓቱ ላይ የሚታዩ የሙስና ተግባራትን ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳኝነት ስርዓቱ ላይ የሚታዩ የሙስና ተግባራትን ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ ይፋ አደረገ። በስትራቴጂው ፋይዳ እና በቀጣይ አተገባበሩ ዙሪያ በማተኮር ከዳኞችና ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።…

በፍሎሪዳ ምንም የማብረር ልምድ የሌለው መንገደኛ በህመም ከወደቀው ፓይለት አውሮፕላኑን ተረክቦ በሰላም ማሳረፍ ቻለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የበረራ ልምድ የሌለው መንገደኛ አውሮፕላኑን በአሜሪካ ፍሎሪዳ አውሮፕላን ማረፊያ አሳረፈ፡፡ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪው ሮበርት ሞርጋን ግለሰቡ ከሚያበረው አውሮፕላን መልዕክት ሰማ ከበሃማስ በኩል፡፡ "አውሮፕላኑን እንዴት እንደማበር ምንም…

በአዲስ አበባ ባለይዞታዎች የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ ማቅረቢያ ቀነ ገደብ ነገ እንደሚጠናቀቅ ኤጀንሲው ገለፀ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በአዲስ አበባ ባለይዞታዎች የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ በተሰጠው የጊዜ ገደብ እንዲያቀርቡ የከተማዋ የመሬት ይዞታ፣ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አሳሰበ፡፡ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ጀማል ሀጅ እንደገለፁት፥ ለይዞታ ማርጋገጫ በተመረጡ…

ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ዩኒቨርሲቲ ለገቡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2013 ዓ.ም ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ወደ ዩኒቨርሲቲ ለገቡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ የገንዘብ ድጋፉ በመዲናዋ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች…

በኢትዮጵያና በብራዚል መካከል የተፈረሙ ስምምነቶችን ተግባራዊነት በመከታተል በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በኢትዮጵያና በብራዚል መካከል የነበረው የዲፕሎማሲ ግንኙነት፣ የተፈረሙ ስምምነቶችና በሂደት ላይ ያሉ ጉዳዮች የአፈፃፀም ደረጃ በተመለከተ ከዘጠኝ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሂዷል። በምክክር መድረኩ የስኳር ኮርፖሬሽን፣…

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅ ተጓዦች ምዝገባ መጀመሩን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅ ምዝገባ መጀመሩን አስታወቀ። በዚህም መሰረት የ2014 ዓ.ም የሐጅ ተጓዦች አጠቃላይ አገልግሎት ዋጋ 83 ሺህ 500 ብር መሆኑን ምክር ቤቱ ያወጣው የዋጋ ዝርዝር…