Fana: At a Speed of Life!

በተያዘው የፈረንጆች ዓመት የተፈጸመው ዓለም አቀፍ የብድር መጠን ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በተያዘው የፈረንጆች ዓመት የተፈጸመው ዓለም አቀፍ የብድር መጠን ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ። እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) መረጃ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እና…

በኮሮና ቫይረስ አመጣጥ ዙሪያ ጥናት የሚያካሂደው ልዑክ ቻይና ገብቷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮሮና ቫይረስ አመጣጥ ዙሪያ ጥናት የሚያካሂደው የዓለም ጤና ድርጅት ልዑክ ቻይና ቤጂንግ ገብቷል። በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ቀውስ እያስከተለ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አመጣጥ ሁኔታ በርካታ ሀገራትን እና ድርጅቶችን ሲያወዛግብ ቆይቷል።…

ጠ/ሚ ዐቢይ ከደቡብ ክልል የፌደራል፣ የክልል እና የዞን አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከደቡብ ክልል የፌደራል፣ የክልል እና የዞን አመራሮች ጋር ተወያዩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአመራሮቹ ጋር በክልሉ ሰላም፣ ልማት፣ የአደረጃጀት ጥያቄዎችና በሃገር ግንባታ ዙሪያ ላይ ነው ውይይት ያደረጉት። በውይይቱ ላይ…

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 7 ሺህ 766 ደርሷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 7 ሺህ 766 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ትናንት በ24 ሰአታት ውስጥ ለ3 ሺህ 922 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 206 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውም አስታውቋል።…

በቀን 1 ነጥብ 2 ሚሊየን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎችን የሚያመርት ፋብሪካ ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ24 ሰአት ውስጥ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ደረጃውን የጠበቀ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎችን ማምረት የሚችል ፋብሪካ ተመርቆ ስራ ጀመረ። ጉያ ሜዲካል ማስክ ማምረቻ የተሰኘው ፋብሪካ ለ450 ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል። በዚሁ የምረቃ ስነ ስርአት ላይ…

በአዲስ አበባ በድምጻዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ስም የተለያዩ የመታሰቢያ ቦታዎች ተሰየሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በድምጻዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ስም የተለያዩ የመታሰቢያ ቦታዎች ተሰየሙ። ለድምፃዊው መታሰቢያዎቹ የተሰየሙለት በአቃቂ ክፍለ ከተማ ገላን አካባቢ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ከኃይሌ ጋርመንት ወደ ጀሞ የሚወስደው መንገድ፣ ቦሌ…

አርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ከመገደሉ በፊት የኦነግ ሸኔ አባላት በአርቲስቱ ቴሌግራም አድራሻ በጽሁፍና በድምፅ የላኩለትን የግድያ ዛቻ በማስረጃነት መያዙ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ከመገደሉ በፊት የኦነግ ሸኔ አባላት በአርቲስቱ ቴሌግራም አድራሻ በጽሁፍና በድምፅ የላኩለትን የግድያ ዛቻ በማስረጃነት  መያዙን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ይፋ አደረገ። አቃቤ ህግ በትናትናው ዕለት በስጠው መግለጫ ÷ ከአርቲስቱ ግድያ…

የአርቲስ ሐጫሉ ሁንዴሳን ስራዎች የሚዘክር ስነ ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአርቲስ  ሐጫሉ ሁንዴሳን ስራዎች የሚዘክር ስነ ስርዓት በአዲስ አበባ ተካሄደ። በሸራተን አዲስ ትላንት ምሽት በተካሄደው ስነ ስርዓት የሙያ አጋሮቹ የአርቲስቱን ስራዎች በማንሳት ለቤተሰቦቹ ያላቸውን አጋርነት አሳይተዋል። አርቲስት አሊ ቢራን…

በአርቲስት ሃጫሉ ግድያ ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው ከበደ ገመቹ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው  ከበደ ገመቹ በቁጥጥር ስር መዋሉን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ። ጠቅላይ አቃቤ ህግ ትናንት ማምሻውን ባወጠው መግለጫ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር የዋለው በአደኣ አካባቢ ልዩ ስሙ ድሬ…

ከ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኞች በስተቀር ሁሉም ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ የትምህርት ደረጃ ያለፈተና እንዲዘዋወሩ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ክልላዊ እና ሀገር አቀፍ ፈተና ወሳጆች በስተቀር ሁሉም የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ የትምህርት ደረጃ ያለምንም ፈተና እንዲዘዋወሩ ተወሰነ። ያለፈተና የተዘዋወሩ ተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት…