ስፓርት
የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ መድን ከ40 ሚሊየን ብር በላይ አገኘ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው የኢትዮያ መድን ከ40 ሚሊየን ብር በላይ አግኝቷል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ከብሮድካስት እና ስም ስያሜ መብት የሚያገኙት ክፍፍል ይፋ አድርጓል።
በዚህም ዓመቱን በአሸናፊነት ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ መድን 40 ሚሊየን 295 ሺህ ብር በላይ ማግኘቱ ተገልጿል።
እንዲሁም በሊጉ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ ቡና 37 ሚሊየን 703 ሺህ ብር ያገኘ ሌላኛው ክለብ እንደሆነ ተመላክቷል።…
Read More...
ባየርን ሙኒክ ሉዊስ ዲያዝን ማስፈረሙን ይፋ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባየርን ሙኒክ ኮሎምቢያዊውን የመስመር አጥቂ ሉዊስ ዲያዝን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡
የጀርመኑ ኃያል ክለብ ባየርን ሙኒክ የ28 ዓመቱን የሊቨርፑል የመስመር አጠቂ ተጫዋች በ65 ነጥብ 5 ሚሊየን ፓውንድ ዋጋ የግሉ አድርጓል።
ኮሎምቢያዊው ተጫዋች በሙኒክ ቤት ለአራት ዓመታት የሚያቆየውን የኮንትራት ውል የፈረመ ሲሆን፤…
ዩራጋይ የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ ያሳካችበት ዕለት…
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዩራጋይ ራሷ ያዘጋጀችውን የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ በፍጻሜው አርጀንቲናን በማሸነፍ ራሷ በማንሳት የመጀመሪያዋ ሀገር የሆነቸው በዛሬዋ ዕለት በፈረንጆቹ 1930 ነበር፡፡
13 ሀገራትን ያሳተፈው የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ በዩራጋይ አስተናጋጅነት በዋና ከተማዋ ሞንቴቪዲዬ ከፈረንጆቹ ሀምሌ 13 እስከ ሀምሌ 30 መካሄዱን ታሪክ…
ማንቼስተር ሲቲ ጀምስ ትራፎርድን አስፈረመ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ሲቲ እንግሊዛዊውን ግብ ጠባቂ ጀምስ ትራፎርድን ከበርንሊ ማስፈረሙን ይፋ አደርጓል፡፡
የ22 ዓመቱ ግብ ጠባቂ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከበርንሊ ጋር በሻምፒዮንሺፑ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡
ክለቡ ከአንድ ዓመት የሻምፒዮንሺፕ ቆይታ በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ቢመለስም ግብ ጠባቂውን ለማንቼስተር ሲቲ አሳልፎ…
ዦአው ፌሊክስ አልናስርን ተቀላቀለ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሳዑዲው ክለብ አልናስር ፖርቹጋላዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ዦአው ፌሊክስ ከቼልሲ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡
የ25 ዓመቱ ተጫዋች በ30 ሚሊየን ዩሮ መነሻ የዝውውር ሂሳብ አልናስርን የተቀላቀለ ሲሆን፥ በሳዑዲ ፕሮ ሊጉ ክለብ እስከ ፈረንጆቹ 2027 የሚያቆየውን ውል ፈርሟል፡፡
ተጫዋቹ ከቼልሲ በተጨማሪ ለኤሲ ሚላን፣…
ሰንደርላንድ ግራኒት ዣካን ለማስፈረም ተስማማ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሰንደርላንድ የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች ግራኒት ዣካን ከባየርሊቨርኩሰን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል፡፡
ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ያደገው ሰንደርላንድ ለግራኒት ዣካ ዝውውር 20 ሚሊየን ዩሮ ወጪ አድርጓል፡፡
የ32 ዓመቱ ተጫዋች በሰንደርላንድ እስከ ፈረንጆቹ 2027 ድረስ የሚያቆየውን የኮንትራት ውል ይፈራረማል፡፡…
አርሰናል ዬከሬሽን ከደጋፊዎቹ ጋር ባስተዋወቀበት ጨዋታ ኒውካስልን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል አዲሱ ፈራሚውን ቪክተር ዮኬሬሽ ከደጋፊዎቹ ጋር ባስተዋወቀበት ጨዋታ ኒውካስል ዩናይትድን 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡
ሁለቱ ክለቦች ባደረጉት የአቋም መፈተሸ ጨዋታ የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ሜሪኖ እና ኦዴጋርድ እንዲሁም መርፊ (በራሱ መረብ ላይ) አስቆጥረዋል፡፡
የኒውካስል ዩናይትድን ግቦች…