Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ለ2025ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ጊኒ እና ታንዛኒያ ጋር ተደለደለች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሞሮኮ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የ2025ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ኢትዮጵያ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ጊኒ እና ታንዛኒያ ጋር ተደልድላለች። የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌደሬሽን ካፍ የ2025ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ምድብ ድልድል ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም መሰረት ካሉት 12 ምድቦች ኢትዮጵያ በምድብ 8 ተደልድላለች። በድልድሉ በአህጉሪቱ የሚገኙ 48 ሀገራት ተጋጣሚዎቻቸውን ማወቃቸውን ከካፍ ቲቪ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Read More...

ሀድያ ሆሳዕና ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሣምንት ጨዋታ መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 1 ረትቷል፡፡ ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ቡና በአንተነህ ተፈራ ጎል ሲመራ ቢቆይም÷ የኋላእሸት ሰለሞን ለሀድያ ሆሳዕና ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች ሽንፈት አስተናግዷል፡፡ ቀደም ብሎ በተካሄደው የ30ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር…

የ2017 የውድድር ዘመን የተጫዋቾች የዝውውር ጊዜ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2017 የውድድር ዘመን የተጫዋቾች የዝውውር ጊዜ ይፋ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታወቀ፡፡ በዚህም መሠረት ከሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም የዝውውር ጊዜው ክፍት ሆኖ ይቆያል መባሉን የፌደሬሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

በዛሬ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ኔዘርላንድስ ትጠበቃለች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ምሽት አንድ ሠዓት ላይ ሮማንያ ከኔዘርላንድስ (ሆላንድ) በአሊያንዝ አሬና ስታዲያም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ የዛሬው የጨዋታ መርሐ-ግብር ሲቀጥልም ምሽት አራት ሠዓት ላይ በሬድቡል አሬና ስታዲያም ኦስትሪያ ከቱርክ ይገናኛሉ፡፡ ምንም እንኳን የቅድመ ጨዋታ ግምቶች…

ፈረንሳይ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ ፈረንሳይ ቤልጂየምን 1 ለ 0 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀሏን አረጋገጠች፡፡ ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ቤልጂየማዊው ተከላካይ ያን ቬርቶገን በራሱ ላይ ባስቆጠራት ግብ ፈረንሳይ 1 ለ 0 አሸንፋለች፡፡ ቀደም ሲሉ በተረደጉ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ስዊዘርላንድ፣ ጀርመን እና ስፔን እ ወደ ቀጣዩ ዙር…

አፍሪካውያኖቹ በስፔን ብሔራዊ ቡድን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጋናውያን ቤተሰቦች የተወለደው ኒኮ ዊሊያምስ እንዲሁም ከኢኳቶሪያል ጊኒ እና ሞሮኮ የዘር ግንድ ካላቸው ቤተሰቦች የተገኘው ላሚን ያማል በአውሮፓ ዋንጫ ከስፔን ብሄራዊ ቡድን ጋር ድንቅ ጊዜን እያሳለፉ ይገኛሉ፡፡ በትናንት ምሽት ስፔን ጆርጂያን 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት ባሸነፈችበት ጨዋታ ኒኮ ዊሊያምስ አንድ ጎል…

በአውሮፓ ዋንጫ ፈረንሳይ ከቤልጂየም የሚያደርጉት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን ፈረንሳይና ቤልጂየም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚህ መሰረትም ምሽት 1 ሰዓት ላይ ፈረንሳይ እና ቤልጂየም በዱሲልዶርፍ አሬና ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ…