Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሐዋሳ ከተማ  አርባምንጭ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የሐዋሳ ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ እስራኤል እሸቱ በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ሐዋሳ ከተማ ተከታታይ ሁለተኛ ድሉን ሲያሳካ፤ አርባምንጭ ከተማ ደግሞ ባለፉት ሦስት ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዷል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ሐዋሳ ከተማ በ34 ነጥብ 12ኛ እንዲሁም አርባምንጭ ከተማ በ35 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ በዕለቱ የመጨረሻ መርሐ ግብር…
Read More...

ካርሎ አንቼሎቲ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጣሊያናዊው ካርሎ አንቼሎቲ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን መሾማቸው ይፋ ሆኗል፡፡ ሪያል ማድሪድ ከሪያል ሶሴዳድ የሚያደርገው የላሊጋው ጨዋታም በማድሪድ ቤት የመጨረሻ ኃላፊነታቸው እንደሚሆን ተገልጿል፡፡ አንቼሎቲ በፈረንጆቹ ግንቦት 26 በይፋ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነታቸውን እንደሚረከቡ ዘ አትሌቲክ…

አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ በባርሴሎና ለመቆየት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባርሴሎናው አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት የሚያቆያቸውን ውል ለመፈረም ከክለቡ ጋር ተስማምተዋል፡፡ ከትናንት ምሽቱ የኤል ክላሲኮ ድል በኋላ ዩዋን ላፖርታን ጨምሮ የክለቡ አመራሮች ከአሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ እና ወኪላቸው ጋር መወያየታቸውን ባርካ ዩኒቨርሳል ምጮቹን ጠቅሶ  ዘግቧል፡፡ ከውይይቱ በኋላም…

ባርሴሎና ሪያል ማድሪድን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ35ኛ ሳምንት የስፔን ላሊጋ ጨዋታ ባርሴሎና ሪያል ማድሪድን 4 ለ 3 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡ በጨዋታው ለባርሴሎና ራፊንሀ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ላሚን ያማል እና ኤሪክ ጋርሺያ  ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ ሪያል ማድሪድን ከሽንፈት መታደግ ያልቻሉ ሶስት ግቦች ፈረንሳዊው የፊት መስመር…

ማንቼስተር ዩናይትድ 17ኛ ሽንፈቱን አስተናገደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ በ2024/25 የውድድር ዘመን 17ኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡ በኦልድትራፎርድ ዌስትሃም ዩናይትድን ያስተናገደው ዩናይትድ ጃሮድ ቦውን እና ቶማስ ሱቼክ ባስቆጠሯቸው ግቦች 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡ በሌሎች የሊጉ 36ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ…

54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሲካሄድ የቆየው 54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በድምር ውጤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊነት ተጠናቅቋል። በሻምፒዮናው በድምር ውጤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ279 ነጥብ አንደኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ፣ መቻል በ242 ነጥብ ሁለተኛ እንዲሁም ሸገር ሲቲ በ143 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ…

ኒውካስል ዩናይትድ ቼልሲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 36ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኒውካስል ዩናይትድ ቼልሲን 2 ለ 0 በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ፡፡ በሴንት ጄምስ ፓርክ በተደረገው ጨዋታ ሳንድሮ ቶናሊ እና ቡሩኖ ጉማሬሽ አስቆጥረዋል፡፡ በጨዋታው የቼልሲው አጥቂ ኒኮላስ ጃክሰን በኒውካስሉ ተከላካይ ሲቬን ቦትማን ላይ በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ…