Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የእርምጃ ውድድር ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታ ወርቅ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በካሜሩን ዱዋላ እየተካሄደ በሚገኘው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የእርምጃ ውድድር ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታዎች የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆናለች፡፡ ዛሬ ረፋድ የተካሄደው የ20 ኪሎ ሜትር የእርምጃ ውድድር በአትሌት ስንታየሁ ማስሬ እና ምስጋና ዋቁማ አሸናፊነት ተጠናቅቋል። እስከ አሁን በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታዎች የእርምጃ ውድድሮች 2 ወርቅ፣ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች 1 ወርቅና 1 ብር፣ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች 1 ወርቅና 1 ብር እንዲሁም በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች 1 ነሐስ…
Read More...

ፈረንሳይ፣ እንግሊዝና ኔዘርላንድስ ጥሎ ማለፉን ለመቀላቀል ብርቱ ፍልሚያ ይጠብቃቸዋል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የዛሬ መርሐ-ግብሮች ጥሎ ማለፉን ለመቀላቀል የሚያስችሉ ጠንካራ ፉክክር የሚጠብቃቸው አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚህ መሠረትም ምሽት 1 ሠዓት ላይ በቡድን አራት የተደለደሉት ፈረንሳይ ከፖላንድ እንዲሁም ኔዘርላንድስ (ሆላንድ) ከኦስትሪያ በተመሳሳይ ሠዓት ይጫወታሉ፡፡ ምድብ አራትን የምትመራው…

በቦስተን የሴቶች 10ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በቦስተን በተካሄደው የሴቶች 10ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እሰከ 3 ደረጃ በመያዝ አሸንፈዋል፡፡ ውድድሩን መልክናት ዉዱ በ31 ደቂቃ ከ15 ሴኮንድ በመጨረስ አንደኛ ደረጃን ስትይዝ ፣ቦሰና ሙላት በ31 ደቂቃ ከ16 ሴኮንድ፣ሰናይት ጌታቸው በ31 ደቂቃ ከ17 ሴኮንድ በመግበት 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ…

“መቻል ለኢትዮጵያ” የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የፊታችን ሰኔ 23 ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) "መቻል ለ ኢትዮጵያ" የተሰኘ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የፊታችን እሑድ ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡ የጎዳ ላይ ሩጫው የመቻል ስፖርት ክለብን 80ኛው ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ነው የሚካሄደው፡፡ መነሻና መድረሻውን መስቀል አዳባባይ በሚያደርገው የሩጫ ውድድር በርካታ ሰዎች…

ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ28ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስን ግብ ኤፍሬም ታምራት(በራስ ላይ) ሲያስቆጥር ÷ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አቻ ያደረገችዋን ግብ ደግሞ ባሲሩ ኡመር ከመረብ አሳርፏል፡፡ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የሚካሄደው የሊጉ…

በአውሮፓ ዋንጫ ጀርመን ከስዊዘርላንድ እንዲሁም ስኮትላንድ ከሀንጋሪ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ ጀርመን ከስዊዘርላንድ እንዲሁም ስኮትላንድ ከሀንጋሪ ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ አዘጋጇ ሀገር ጀርመን ከሰዊዘርላንድ ጋር የምታደርገው ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በፍራንክፈርት አሬና ስታዲየም ይደረጋል፡፡ ሁለት የምድብ ጨዋታዎችን ያሸነፈው የጀርመን ብሄራዊ ቡድን…