Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ባሕርዳር ከተማ አዳማ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ28ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባሕርዳር ከተማ ከመመራት ተነስቶ አዳማ ከተማን 3 ለ 2 ማሸነፍ ችሏል፡፡ ኤልያስ ለገሠ እና ዮሴፍ ታረቀኝ ለአዳማ ከተማ እንዲሁም የአብሥራ ተስፋዬ፣ ወንድወሰን በለጠ እና ፍቅሩ ዓለማየሁ (በራስ ላይ) ለጣና ሞገዶቹ ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ-ግብር ሲቀጥል 12 ሠዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና ይጫወታሉ፡፡
Read More...

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፍሬወይኒ የ1500 ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፍሬወይኒ ሐይሉ በፖላንድ በተካሄደው የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ የሴቶች ሩጫ ውድድር አሸንፋለች፡፡ አትሌቷ በፖላንድ ባይድጎሽ ከተማ በተካሄደው የ1500 የሴቶች ሩጫ ውድድር 3፡58.59 በሆነ ሰዓት በመግባት ማሸነፏን ከዎርልድ አትሌቲክስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ከዚህ በፊት አትሌቷ በፖላንድ…

በአውሮፓ ዋንጫ ስሎቬኒያና ሰርቢያ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ 3 ጨዋታ ስሎቬኒያና ሰርቢያ 1 አቻ ተለያዩ፡፡ የስሎቬኒያን ጎል ዛን ካርኒቺኒክ (69') ሲያስቆጥር ሰርቢያን አቻ ያደረገችውን ደግሞ ሉካ ጆቪች (90'+5) ከመረብ አገናኝቷል፡፡

በአውሮፓ ዋንጫ ስፔን እና ጣልያን የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ሁለተኛው ዙር የምድብ ማጣሪያ መርሐ ግብር ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚህ መሰረትም በምድብ ሁለት የሚገኙት ጣልያን እና ስፔን ምሽት 4 ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡ በመጀመሪያው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ጣልያን አልባንያን 2 ለ 1 እንዲሁም ስፔን ክሮሺያን 3 ለ 0…

ክሮሺያ እና አልባኒያ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ክሮሺያ እና አልባኒያን ሁለት አቻ ተለያይተዋል፡፡ የአልባኒያን ጎል ላቺ በ11ኛው እና ጋሱላ በ95ኛው ደቂቃ ከመረብ ሲያሳርፉ÷ የክሮሺያን ጎሎች ደግሞ ክራማሪች በ74ኛው እና ጋሱላ (በራስ ላይ) በ76ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡ በመጀመሪያው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ክሮሺያ በስፔን 3 ለ 0…

አስተናጋጇ ጀርመን ዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዋን ታደርጋለች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት የመጀመሪያው ዙር የምድብ ማጠሪያ መጠናቀቁን ተከትሎ ዛሬ ሁለተኛው ዙር የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ይጀመራል፡፡ በዚህም ባለፈው በስፔን 3 ለ 0 የተሸነፈችው ክሮሺያ በጣልያን 2 ለ 1 ከተረታችው አልባኒያ ጋር ቀን 10 ሠዓት ላይ ይጫወታሉ፡፡ እንዲሁም ምሽት 1 ሠዓት ላይ አስተናጋጇ ጀርመን ከሀንጋሪ የሚያደርጉት ጨዋታ…

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ካሜሩን አቀና

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ወደ ካሜሩን ዱዋላ አቀና፡፡ 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በካሜሩን አስተናጋጅነት በዱዋላ እንደሚካሄድ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡ የኢትዮጵያ ልዑክም ዛሬ ጠዋት ወደ ካሜሩን ያቀና ሲሆን÷ የኢትዮጵያ…