ስፓርት
ሲዳማ ቡና በኢትዮጵያ ዋንጫ ለፍጻሜ አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ሲዳማ ቡና መቻልን በመለያ ምት 7 ለ 6 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና በፍፃሜው ከወላይታ ድቻ ጋር ይገናኛል፡፡
ወላይታ ድቻ ትናንት በግማሽ ፍፃሜው ሸገር ከተማን በማሸነፍ ለፍጻሜ መብቃቱ ይታወቃል፡፡
የዛሬው የሲዳማ ቡና እና መቻል ጨዋታ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ያለምንም ግብ ነበር የተጠናቀቀው፡፡
በኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን የሚሆነው ክለብ በቀጣዩ ዓመት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ላይ ተሳታፊ ይሆናል፡፡
Read More...
በጃፓን በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ዳዊት ወልዴ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጃፓን ጊፉ ከተማ በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ዳዊት ወልዴ አሸንፏል፡፡
ውድድሩን 1፡00፡06 በሆነ ሰዓት በመግባት በአንደኝነት ያጠናቀቀው አትሌት ዳዊት ወልዴ፤ በውድድሩ ሲሳተፍ የመጀመሪያው እንደሆነ ተገልጿል።
በሴቶች በተካሄደው ውድድር ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ ጎይተይቶም ገብረስላሴ 1:08:29…
በሴቶች የለንደን ማራቶን አትሌት ትዕግስት አሰፋ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ45ኛው የለንደን ማራቶን በሴቶች ምድብ የፓሪስ ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በአንደኝነት አጠናቅቃለች፡፡
አትሌት ትግስት ርቀቱን ለመጨረስ 2 ሠዓት ከ15 ደቂቃ ከ50 ሠከንድ ፈጅቶባታል፡፡
በዚሁ ውድድር መርሐ-ግብር ኬንያዊቷ አትሌት ጄፕኮስፔ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ሲፋን ሀሰን ሦስተኛ…
ሊቨርፑል ሻምፒየንነቱን ቀድሞ ለማረጋገጥ አንድ ነጥብ ብቻ…
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ34ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የሊጉ መሪ ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሮድ ምሽት 12 ሠዓት ከ30 ቶተንሃም ሆትስፐርን ያስተናግዳል።
ሊጉን በ79 ነጥብ እየመራ የሚገኘው ሊቨርፑል ከዛሬው ጨዋታ አንድ ነጥብ ካገኘ ቀሪ አራት ጨዋታዎች እየቀሩት ሻምፒየን መሆኑን ያረጋግጣል።
ተጋጣሚው ቶተንሃም ሆትስፐር…
ማንቼስተር ሲቲ ከኖቲንግሀም ፎረስት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ከኖቲንግሃም ፎረስት ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ማንቼስተር ሲቲ የውድድር ዓመቱን ያለ ዋንጫ ላለማጠናቀቅ በዋንጫ ፉክክር ውስጥ ለመቆየት ይፋለማል።
ማንቼስተር ሲቲ በሩብ ፍፃሜው ቦርንመዝን በማሸነፍ ለግማሽ ፍፃሜው ሲበቃ ኖቲንግሀም…
ክሪስታል ፓላስ አስቶን ቪላን በማሸነፍ ለኤፍ ኤ ካፕ ፍጻሜ አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ የኤፍ ኤ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ አስቶን ቪላን 3 ለ 0 በማሸነፍ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
ምሽት 1፡15 በዌንብሌይ በተደረገው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ የፓላስን የማሸነፊያ ግቦች ኤቤርቺ ኤዜ እና ኢስማኤላ ሳር (2) አስቆጥረዋል፡፡
በሌላ የግማሽ ፍጻሜ መርሐ…
ወላይታ ድቻ በኢትዮጵያ ዋንጫ ለፍጻሜ አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ሸገር ከተማን 2 ለ 0 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ወደ ፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል፡፡
ወላይታ ድቻ ለቀጣዩ የውድድር ዓመት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደገውን ሸገር ከተማን ባሸነፈበት ጨዋታ ዘላለም አባተ እና ብዙዓየሁ ሰይፈ የማሸነፊያ ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡…