Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሊድስ ዩናይትድ እና በርንሌይ ወደ ፕርሚየር ሊጉ አደጉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሊድስ ዩናይትድ እና በርንሌይ ለ2025/26 የውድድር ዓመት ከሻምፒዮን ሺፕ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ዛሬ በተደረገ የሻምፒዮን ሺፕ ጨዋታ በርንሌይ ሼፍልድ ዩናይትድን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ በርንሌይ ነጥቡን 94 በማድረስ ለቀጣዩ የውድድር ዓመት ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል። በተመሳሳይ ሊድስ ዩናይትድ ስቶክ ሲቲን በማሸነፍ ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ያደገ ሌላኛው ቡድን መሆን ችሏል፡፡ በዚህም ከሁለት…
Read More...

ባሕርዳር ከተማ መቐለ 70 እንደርታን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ባሕርዳር ከተማ መቐለ 70 እንደርታን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የባሕርዳር ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ቸርነት ጉግሳ እና አቤል ማሙሽ በተመሳሳይ ሁለት ሁለት ግቦችን ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ መቐለ 70 እንደርታን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ አሸናፊ…

መቻል አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ መቻል አዳማ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የመቻልን ሁለቱንም የማሸነፊያ ግቦች ሽመልስ በቀለ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቅቆ በተጨመረ ደቂቃ እና በ49ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል። ውጤቱን ተከትሎ መቻል በ38 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ አዳማ ከተማ ደግሞ…

አርሰናል ሲያሸነፍ ማንቼስተር ዩናይትድ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 33ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ከሜዳው ውጪ ኢፕስዊች ታውንን ሲያሸንፍ ማንቼስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡ ቀን 10 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ አርሰናል ኢፕስዊች ታውንን 4 ለ 0 አሸንፏል፡፡ አርሰናል የጨዋታ ብልጫ በወሰደበት ጨዋታ ሊያንድሮ ትሮሳርድ (2)፣ ጋብርኤል ማርቲኔሊ…

ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ 26ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 9 ሠዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል። የሊጉ ጨዋታ አመሻሽ 12 ሠዓት ላይ ቀጥሎ ሲካሄድ አርባ…

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግቦች፤ ቢንያም ፍቅሩ (2) እና አብዱ ሳሚዮ ሲያስቆጥሩ፤ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ግብ ደግሞ ቡልቻ ሹራ ከመረብ አሳርፏል፡፡…

ማንቼስተር ሲቲ ኤቨርተንን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ኤቨርተንን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የማንቼስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኦ-ሬልይ እና ኮቫቺች ማስቆጠር ችለዋል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ማንቼስተር ሲቲ በ58 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ ኤቨርተን በ38 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ…