ስፓርት
ኬፕ ቨርዴ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች
አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ኬፕ ቨርዴ ሞሪታኒያን በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች፡፡
ምሽት 2 ሰዓት በተደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ኬፕ ቨርዴ ሪያን ሜንዴዝ ባለቀ ደቂቃ ባስቆጠራት የፍጹም ቅጣት ምት 1 ለ 0 አሸንፋለቸ፡፡
ውጤቱን ተከትሎም ኬፕ ቨርዴ በታሪኳ ለ2ኛ ጊዜ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀል ችላለች፡፡
Read More...
በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ሲያሸንፍ ወላይታ ድቻና ሃድያ ሆሳዕና አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ወልቂጤ ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አንተነህ ተፈራ በ33ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ…
የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ሀገር አቀፍ የችቦ ቅብብሎሽ በመቀሌ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ሀገር አቀፍ የችቦ ቅብብሎሽ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በመቀሌ ከተማ ተከሂዷል።
በችቦ ቅብብሎሽ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።
መርሐ-ግብሩ በመጪው ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ለሚካሄደው…
አንጎላ ናሚቢያን በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜው ተቀላቀለች
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ አንጎላ ናሚቢያን 3 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜው ገብታለች፡፡
ምሽት 2 ሰዓት ላይ በቡዋኬ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አዲልሰን ነቡላ፣ ጊልሰን ዳላ እና ኦገስቲኖ ሙቡሉ ለአንጎላ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡
በጨዋታው የአንጎላው ግብ ጠባቂ አዲልሰን ኔብሉ እና የናሚቢያው…
ቅዱስ ጊዮርጊስ በድሬዳዋ ከተማ 3 ለ 0 ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሳይጠበቅ በድሬዳዋ ከተማ 3 ለ 0 ተሸንፈዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ኤፍሬም አሻሞ፣ ቻርለስ ሙሲጌ እና ሱራፌል ጌታቸው የድሬዳዋን ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም ድሬዳዋ ነጥቡን 14 በማድረስ ለጊዜው 10ኛ ደረጃ ላይ…
አትሌት ሳሙኤል ተፈራ በአስታና የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሻምፒዮና አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ሳሙኤል ተፈራ በካዛኪስታን አስታና በተካሄደ የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የአመቱን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል፡፡
አትሌቱ 7 ደቂቃ ከ33 ሴኮንድ ከ85 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት ነው የዓመቱን የ3 ሺህ ሜትር ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ማሸነፉን የዓለም አትሌቲክስ መረጃ ያመላከተው፡፡
የ3 ሺህ ሜትር…
ታላቁ የወንጪ 10 ኪሎ ሜትር ሩጫ በወንጪ ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ታዋቂ አትሌቶች የተሳተፉበት ታላቁ የወንጪ 10 ኪሎ ሜትር ሩጫ በወንጪ ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ተካሄደ፡፡
በውድድሩ በሴቶች ጌጤ አለማየሁ፣ ፎትን ተስፋዬ እና ኑሪት አህመድ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ በቀዳሚነት አጠናቀዋል።
በወንዶች ደግሞ አትሌት አዲሱ ነጋሽ፣ ሞገስ ንኡማንና ኤሊያስ ጫኔ ተከታትለው በመግባት…