ስፓርት
ኧርሊንግ ሃላንድ የኖርዌይ ብሄራዊ ቡድን የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኖርዌጂያኑ የማንቼስተር ሲቲ አጥቂ ኧርሊንግ ሃላንድ በ36 ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ባስቆጠራቸው ግቦች የሀገሩ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ለመሆን በቅቷል፡፡
የ24 ዓመቱ አጥቂ ትናንት ምሽት በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ጨዋታ ኖርዌይ ስሎቫኒያን 3 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ 2 ግቦችን በማስቆጠር ሪከርዱን የግሉ ማድረግ ችሏል፡፡
ሃላንድ በአጠቃላይ በ36 ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች 34 ግቦችን በማስቆጠር ነው ለ90 ዓመታት በሀገሩ ልጅ ጆርገን ጁቬ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ያሻሻለው፡፡
በፈረንጆቹ…
Read More...
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የብስክሌት ሻምፒዮና 3ኛውን የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ ኤልዶሬት እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ የብስክሌት ሻምፒዮና ድብልቅ ውድድር ኢትዮጵያ 3ኛውን የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች።
የአፍሪካ የብስክሌት ሻምፒዮና በኬንያ ኤልዶሬት ከትናንት ጀምሮ እየተካሄደ እንደሚገኝ የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
የቀድሞ የሼፊልድ ዩናይትድ ተከላካይ ጆርጅ ባልዶክ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የሼፊልድ ዩናይትድ ተከላካይ እና አሁን ላይ ለግሪኩ ፓናቲናይኮስ በመጫወት ላይ የነበረው ጆርጅ ባልዶክ በ31 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
ባልዶክ አቴንስ በሚገኘተው መኖሪያ ቤቱ መዋኛ ገንዳ ውስጥ ሕይወቱ አልፎ መገኘቱ ተነግሯል፡፡
ፖሊስ የተጫዋቹን ሞት መንስኤ እያጣራ እንደሚገኝ መግለጹን ቢቢሲ…
ከ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በደቡብ ሱዳን ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ማጣርያ ውድድር ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን 2 ለ 1 ተሸነፈች፡፡
ለደቡብ ሱዳን ግቦቹን ንጎንግ ጋራንግ እና ዳንኤል ቢቺኦክ ሲያስቆጥሩ÷ ኢትዮጵያን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ዋንጫ ቱት ከመረብ አሳርፏል፡፡
በአፍሪካ የብስክሌት ሻምፒዮና የመጀመሪያ ቀን ውድድር ኢትዮጵያ 2 የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ እየተካሄደ በሚገኘው የ2024 የአፍሪካ የብስክሌት ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን ብስክሌተኞች ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው አስገኝተዋል፡፡
ሜዳሊያዎቹ የተገኙት በጽጌ ካህሳይ እና ምዕራፍ ገ/እግዚአብሔር መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
ኤሊዩድ ኪፕቾጌ በድጋሚ የዩኔስኮ የስፖርት አምባሳደር ሆነ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁለት ጊዜ የኦሊፒክ ሻምፒዮኑ ኤሊዩድ ኪፕቾጌ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የስፖርት አምባሳደር ሆኗል፡፡
ኬኒያዊው የማራቶን ባለታሪክ ኤሊዩድ ኪፕቾጌ ለሁለት ዓመታት ነው የስፖርት አምባሳደር በመሆን የተሰየመው፡፡
የ39 ዓመቱ አትሌት በስፖርት ዘርፍ ላሳየው ዲሲፕሊን እና…
በሞሮኮ የእጅ ኳስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሶስት ክለቦች ትወከላለች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሞሮኮ ላዩን ከተማ በሚካሄደው 45ኛው የአፍሪካ ክለቦች የወንዶች እና ሴቶች እጅ ኳስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሶስት ክለቦችን እንደምታሳትፍ ተገለፀ፡፡
በዚህም መሰረት መቻል፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ እጅ ኳስ ክለቦች በመድረኩ ኢትዮጵያን በመወከል ይሳተፋሉ።
በወጣው ምድብ መሰረትም መቻል እጅ ኳስ…