ስፓርት
በኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ፋሲል ከነማና ሐዋስ ከተማ አሸንፈዋል
አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ፋሲል ከነማ እና ሐዋስ ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ የተካሄደው የሐዋሳ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ ጨዋታ በሐይቆቹ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
አሊ ሱሌማን የሐዋሳ ከተማን ሁለት ጎሎች ሲያስቆጥር አቡበከር ሳኒ የወልቂጤ ከተማን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል፡፡
ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተካሄደ ሌላኛ መርሃ ግብር ፋሲል ከነማ በጌታነህ ከበደ ጎሎች ሻሸመኔ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ውጤቱን ተክትሎም አፄዎቹ በ21 ነጥብ…
Read More...
በእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ ሲያሸንፍ ቼልሲ በሜዳው ተሸንፏል
አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ ዌስትሃም ዩናይትድን ሲያሸንፍ ቼልሲ በሜዳው በዎልቭስ ተሸንፏል፡፡
ዌስትሃምን የገጠመው ማንቼስተር ዩናይትድ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ራስመስ ሆይለንድ እና አሊሃንድሮ ጋርናቾ (ሁለት) ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡
ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ የቻለው ማንቼስተር ዩናይትድ ነጥቡን…
53ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል
አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 53ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል፡፡
በሻምፒዮናው በካሜሮን በሚካሄደው 23ኛው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና እና በጋና አክራ በሚካሄደው የመላው አፍሪካ ውድድር እንዲሁም በፓሪስ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ አትሌቶ ተለይተውበታል፡፡…
ብራይተን ክርስታል ፓላስን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ23ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ብራይተን ክርስታል ፓላስን 4 ለ1 አሸንፏል፡፡
ምሽት 12፡00 ሠዓት ላይ በተካሄዱ ጨዋታወች÷ ኒውካስል ከሉተን ታውን 4 አቻ እንዲሁም በርንሌይ ከፉልሀም 2 አቻ ተለያይተዋል፡፡
የዛሬውን ጨዋታ ውጤት ተከትሎም ብራይተን በ35 ነጥብ 7ኛ፣ ኒውካስል በ33 ነጥብ 9ኛ፣ ፉልሀም በ26…
ቶተንሀም እና ኤቨርተን አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ23ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቶተንሀም ከኤቨርተን 2 አቻ ተለያይተዋል፡፡
ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሪቻርልሰን በ4ኛው እና በ41ኛው ደቂቃ የቶተንሀምን ሁለት ጎሎች አስቆጥሯል፡፡
እንዲሁም የኤቨርተንን ጎል ሀሪሰን በ30ኛው እና ብራዝዌት በ94ኛው ደቂቃ ማስቆጠር ችለዋል፡፡
ቶተንሀም በ44 ነጥብ 4ኛ…
መቻል ሲዳማ ቡናን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ መቻል ሲዳማ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
መቻል ማሸነፉን ተከትሎ የሊጉን መሪነት ተረክቧል፡፡
የመቻልን የማሸነፊያ ግቦች ምንይሉ ወንድሙ እና አበባየሁ ዮሐንስ (በራሱ ላይ) ሲያስቆ ጥሩ ለሲዳማ ቡና ቡልቻ ሹራ አስቆጥሯል።
ምሽት 12፡00 ሠዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ አዳማ…
ዛሬ ሁለት የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው ሲካሄዱ ማሊ ከኮትዲቯር እንዲሁም ኬፕ ቨርዴ ከደቡብ አፍሪካ ይገናኛሉ፡፡
ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ በሚደረገው ፍልሚያ ማሊ ከአስተናጋጇ ኮትዲቯር ምሽት 2፡00 ሠዓት ላይ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ የወጣው መርሐ-ግብር ያስረዳል፡፡
እንዲሁም ኬፕቨርዴ ከደቡብ አፍሪካ…